Tuesday, August 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናወደ ኢትዮጵያ የፈለሱ ስደተኞች ቁጥር ከ800 ሺሕ በላይ ሆነ

  ወደ ኢትዮጵያ የፈለሱ ስደተኞች ቁጥር ከ800 ሺሕ በላይ ሆነ

  ቀን:

  – የዓለም አቀፍ የስደተኞች ኮሚሽን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ጠይቋል

  ከጎረቤት አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር እያሻቀበ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. 2017 ከገባ ወዲህ የስደተኞች አጠቃላይ ቁጥር 801,079 መድረሱን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

  ኮሚሽኑ በተገባደደው ሳምንት ባወጣው ወርኃዊ ሪፖርት እንደገለጸው፣ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት የመጀመሪያ ወር ብቻ ወደ 8,085 የሚሆኑ ስደተኞች ከተለያዩ የጎረቤት አገሮች ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 3,062 የሚደርሱ ሶማሊያውያን መሆናቸውንና በዶሎ አዶ መጠለያ እንደሚገኙ የኮሚሽኑ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

  እንደ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጠለሉት ስደተኞች የወጣት ስደተኞች ቁጥር ብቻ ወደ 130 ሺሕ ሲጠጋ፣ ከ43 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ያለወላጅና ረዳት ብቻቸውን የተሰደዱ ሕፃናት ናቸው፡፡

  ስደተኞቹ የመጡባቸው አገሮች ስብጥርም ሲታይ 324,591 ደቡብ ሱዳናውያን፣ 245,272 ሶማሊያውያን፣ 165,525 ኤርትራውያን፣ 40,519 ሱዳናውያን፣ 1,611 የመናውያን፣ እንዲሁም ከ5,561 በላይ የሚሆኑት የተለያዩ አገሮች ዜግነት ያላቸው እንደሆኑ በኮሚሽኑ ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

  ለእነዚህም ስደተኞች ማቆያ የሚሆን ከ307.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም አስቸኳያ ምላሽ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

  የጋምቤላ ክልል ወደ 330,290 ስደተኞችን በማስጠለል ቀዳሚውን ሥፍራ ሲይዝ፣ 241,700 የሚጠጉ ስደተኞችን በማስጠለል ደግሞ የሶማሌ ክልል ተከታዩን ሥፍራ ይዟል፡፡ ትግራይ 34,478፣ አፋር 34,012 የሚደርሱ ስደተኞችን እያስተናገዱ ነው ተብሏል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም እንዲሁ ከ19,977 በላይ ስደተኞች እንደሚኖሩ መረጃው ያሳያል፡፡

  ስደተኞቹ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተሠሩ መጠለያዎች ውስጥ ሆነው በዓለም አቀፍ ስደተኞች ኮሚሽን፣ በፌዴራል ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ባለሥልጣን ሥር እየተዳደሩ ይገኛሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

  ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ የአገሪቱ...

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...