Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየተቋረጠው መልሶ ማልማት 78 ሔክታር ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮችን በማፍረስ ሊጀመር...

  የተቋረጠው መልሶ ማልማት 78 ሔክታር ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮችን በማፍረስ ሊጀመር ነው

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነዋሪዎች በተደጋጋሚ በቀረበ ቅሬታ ምክንያት፣ በጊዜያዊነት ለሁለት ዓመታት ያቋረጠውን የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ በድጋሚ ለመጀመር ተዘጋጀ፡፡ በዚህም መሠረት 78 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮች ይፈርሳሉ፡፡

  የከተማው አስተዳደር ነባር መንደሮቹን በተያዘው በጀት ዓመት በማፍረስ ለመልሶ ማልማት ሥራዎች እንዲመች፣ ከነዋሪዎች ንክኪ ነፃ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የበጀት ዓመቱ ከተጀመረ አምስት ወራት ቢቆጠሩም፣ በቀጣዮቹ ወራት በመሀል አዲስ አበባ የሚገኙትን አምስት ነባር መንደሮችን እንደሚያፈርስ አስታውቋል፡፡

  በዚህ መሠረት ፈራሾች የሆኑት መንደሮች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ ቁጥር ሦስት (ከቶታል ማደያ ፊት ለፊት)፣ አራዳ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ግቢ ቁጥር ሁለትና ገዳም ሠፈር፣ የካ ክፍለ ከተማ ሾላና መገናኛ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ደግሞ ጌጃ ሠፈር ናቸው ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡

  የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እነዚህ መንደሮች በጠቅላላው 78 ሔክታር ስፋት አላቸው፡፡ ‹‹አሮጌዎቹን መንደሮች አፍርሶ አዲስ ልማት ለማካሄድ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ያልተቋረጠ የመልሶ ማልማት ሲካሄድ ቆይቷል፣ ነገር ግን ከ2008 ዓ.ም. ወዲህ ነዋሪዎች ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን በማንሳታቸው፣ የከተማው አስተዳደርም ይህንን ቅሬታ በመቀበሉ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ወስኖ ነበር፡፡

  በተለይ ከነዋሪዎች ሲነሳ የቆየው ቅሬታ መሠረታዊ በመሆኑ፣ አስተዳደሩ በመልሶ ማልማት ቦታዎች የሚነሱ ነዋሪዎች የሚስተናገዱበትን መመርያ ለማስተካከል ተገዷል፡፡

  በዚህ መሠረት የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር መመርያ ቁጥር 3/2007፣ እንዲሁም የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍና ለማስተዳደር የወጣውን መመርያ ቁጥር 1/2008 በድጋሚ አሻሽሏል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣው የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅድ አንድ ሺሕ ሔክታር መሬት በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ማልማት ነበር፡፡ ይህ ማለት በየዓመቱ 200 ሔክታር ለማልማት ቢታቀድም ዕቅዱ ግን እንዳልተሳካ ተገልጿል፡፡

  ለዕቅዱ አለመሳካት ምክንያት የሆኑት የቀበሌ ቤት እጥረት፣ ምትክ ኮንዶሚኒየምና ቦታ አለማቅረብ፣ በአመራሮችና በሠራተኞች የሚታየው የማስፈጸም አቅም ብቃት ማነስ፣ እንዲሁም የካሳ ግምት አነስተኛ መሆንና የይገባኛል ክርክር ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

  እነዚህ መመርያዎች በመሻሻላቸውና ማልማት ለሚችሉ ተነሽዎች ቅድሚያ የሚሰጥ በመሆኑ ፕሮግራሙ በድጋሚ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...