Thursday, August 11, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየመንግሥት ተቋማት ለሚያጠቡ ሴት ሠራተኞች ልዩ ቦታ እንዲያዘጋጁ ሕግ ሊወጣ ነው

  የመንግሥት ተቋማት ለሚያጠቡ ሴት ሠራተኞች ልዩ ቦታ እንዲያዘጋጁ ሕግ ሊወጣ ነው

  ቀን:

  በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተቀጥረው ለሚያገለግሉ ሴት ሠራተኞች፣ ከወሊድ በኋላ ጡት የሚጠቡ ልጆቻቸውን መንከባከብ የሚችሉበት የአገልግሎት መስጫ ክፍል እንዲዘጋጅ የሚያደርግ ሕግ እንደሚወጣ ተገለጸ፡፡

  ማንኛውም ሕፃን የእናት ጡት እንዲያገኝም ሆነ እንክብካቤ እንዲደረግለት ማድረግ የሰብዓዊ መብት አንድ አካል ተደርጎ እንደሚወሰድ፣ ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በፀደቀው ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት የትግበራ ዕቅድ ውስጥ ተካቷል፡፡

  የትግበራ ዕቅዱን ለማፅደቅ የሕግ፣ የፍትሕና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሥላሴ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ከሚሆኑት መካከል፣ በሁሉም የመንግሥት ተቋማት እናቶች የሚያጠቡበት አገልግሎት መስጫ ክፍል እንዲኖር ይደረጋል ብለዋል፡፡

  የዚህ ዓይነቱን አገልግሎት ለመስጠት መታሰቡን በበጎ እንደሚያዩት የገለጹት የምክር ቤቱ አባላት፣ በግል ተቋማት ለምን እንደማይጀመር ጠይቀዋል፡፡

  ከአባላት ለተነሱት ጥያቄ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጴጥሮስ፣ ቀደም ብሎ የግል ተቋማትንም ማካተት እንደሚገባ ውይይት ተደርጎ እንደነበር በማስታወስ ለጊዜው በመንግሥት ተቋማት ተጀምሮ፣ በሒደት የግል ተቋማትም በዚሁ ሥርዓት መካተታቸው እንደማይቀር ገልጸዋል፡፡

  ‹‹በመጀመሪያ ሰብዓዊ መብትን የማስከበርና የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለው በመንግሥት ላይ ነው፡፡ ይህንን ኃላፊነት ለማስፈጸም ያለውንም ሕግ እስከ ማሻሻል ድረስ ዕርምጃ ተወስዷል፡፡ ለጊዜው የሕፃናት ማጥቢያን በተመለከተ ቅድሚያ ኃላፊነቱን በመውሰድ መተግበር ከቻለ ቀጥሎ ወደ ግል ተቋማት ማስፋፋት ይቻላል፤›› ሲሉ አቶ ጴጥሮስ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

  የዓለም የጤና ድርጅት በማንኛውም ተቋማት እናቶች ቢያንስ ለስድስት ወራት ጨቅላ ሕፃናትን ጡት እንዲያጠቡ ሲያስብ፣ በአባል አገሮች ተቀጥረው የሚሠሩ እናቶች ልጆቻቸውን በሥራ ቦታ ማጥባት እንደሚገባቸው ያስታውቃል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...