Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች የሚቀርቡበት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በአራት ክልሎች በ5.7 ቢሊዮን ብር እየተገነቡ ለሚገኙት አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች ማቅረብ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

  አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ እየተገነቡ ያሉት በኦሮሚያ ክልል ቡልቡላ፣ በአማራ ክልል ቡሬ፣ በደቡብ ክልል ይርጋለምና በትግራይ ክልል ሁመራ አካባቢዎች ነው፡፡

  እነዚህ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታቸው ሲጠናቀቅ የሚያስፈልጋቸው የግብርና ምርት፣ ሳይስተጓጎል በጥራትና በብዛት ማምረትና ማቅረብ እንዲቻል ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

  በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር የወተት ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ተካ ለሪፖርተር እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በወተት፣ በማር፣ በሥጋና በዶሮ ልማት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ቀርጿል፡፡

  ‹‹በአሁኑ ወቅት ስትራቴጂውን ለመተግበር የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በኦሮሚያ ለሚገነባው ቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የቢዝነስ ፕላን ተዘጋጅቷል፤›› ሲሉ አቶ ታሪኩ አስረድተዋል፡፡

  የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒቴርም እንዲሁ በጥራጥሬ፣ በቅባት እህሎች፣ በአትክልትና በፍራፍሬ ልማት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

  በእርሻ ዘርፍ የተዘጋጀው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እንደየአካባቢው ሥነ ምኅዳር የሚለያይ ሲሆን፣ በሁመራ የሚገነባው አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የቅባት እህሎች (ሰሊጥ) ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ እያሱ አብረሃ (ዶ/ር) ሰሞኑን በተካሄደው አንድ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ በቡሬ እየተቋቋመ ባለው አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚቋቋም አንድ የዘይት ፋብሪካ ብቻ፣ ሁለት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን (20 ሚሊዮን ኩንታል) የቅባት እህል ይፈልጋል፡፡ በአገር ደረጃ እየተመረተ ያለው የቅባት እህል ግን ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ብቻ መሆኑን፣ ‹‹ስለዚህ በርካታ ምርት በጥራት ማምረት ይጠበቅብናል፤›› ብለዋል፡፡

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች