Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሠረታዊ የመዋቅር ለውጡ ቻርተሩን ሊያሻሽል ነው

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሠረታዊ የመዋቅር ለውጡ ቻርተሩን ሊያሻሽል ነው

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያካሄደውን የመዋቅር ጥናት ተግባራዊ ለማድረግ ቻርተሩን ለሦስተኛ ጊዜ ማሻሻል ግድ ነው አለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው መሠረታዊ የመዋቅር ለውጥ ለማካሄድ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ከ60 ዓለም አቀፍ ከተሞች አሠራር ልምድ ለመውሰድ ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱንም ገልጿል፡፡

  ይህንን ጥናት መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር 361/1995 ዓ.ም. ጨምሮ፣ የከተማው ምክር ቤትና የዳኝነት አካላት ሥልጣንና ኃላፊነት ላይ ማሻሻያ ማድረግ የሚያስችል ጥናት አዘጋጅቷል፡፡

  በጥናቱ ላይ እንደተገለጸው 138 መቀመጫዎች ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሕግ የማውጣት ሥልጣኑ በቻርተሩ ላይ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲሆን መገደቡ አግባብ አይደለም፡፡ በዚህም ምክር ቤቱ የከተማውን ዕድገትና ተለዋዋጭ ሁኔታ እየተከታተለ ሕግ እንዳያወጣ እንዳደረገው ጥናቱ ያስረዳል፡፡

  ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማን በሚመለከት ሕግ የማውጣት ጥቅል ሥልጣን ለከተማው ምክር ቤቱ ቢሰጥ፣ የፌዴራል መንግሥት አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሊሰርዘው እንደሚችል ቢመለከት መልካም እንደሆነ አመልክቷል፡፡

  ከምክር ቤቱ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ምክር ቤቱ ሥልጣን ባልሰጠው ጉዳይ ላይ ደንብ እያወጣ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ ይህ አግባብ አለመሆኑን ጥናቱ አመልክቶ፣ ከዚህ በላይ ካቢኔው እስከ ታች ድረስ ወርዶ ቢሮዎች ሊያወጡ የሚገባቸውን መመርያዎች ሲያወጣ እንደሚስተዋል አመልክቷል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፌዴራል መንግሥት ሕግጋት ጋር የሚቃረኑ ሕጎችን ማፅደቁም ተመልክቷል፡፡ ለአብነትም ቀበሌን በወረዳ ለመተካት የወጣው ደንብ ቁጥር 21/2002፣ የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ ከደንብ ቁጥር 54/2005 እንደሚቃረን ጥናቱ ያስረዳል፡፡

  የአዲስ አበባ መዋቅር ጥናትና አደረጃጀት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ያካሄደው ጥናት እንደሚያብራራው፣ የክፍላተ ከተሞች ምክር ቤቶች እንዲቀሩና የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የወረዳ ምክር ቤቶች ብቻ እንዲኖሩ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

  የሕዝቡን ተሳትፎና ተደራሽነት ለማጠናከር ምክር ቤቶቹ በሁለት እርከን ላይ ብቻ ቢዋቀሩ መልካም ነው በማለት ጥናቱ ገልጾ፣ የወረዳ ምክር ቤት አባላት በቀጥታ በሕዝብ የሚመረጡ ስለመሆናቸው በሕጉ ላይ ሊካተት እንደሚገባው አስምሮበታል፡፡

  ይህ ጥናት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በሁለት ደረጃ (እርከን) ብቻ የተዋቀሩ በመሆናቸው፣ በባለጉዳዮች የይግባኝ መብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ሲል ገልጿል፡፡ ጥናቱ የከተማው አስተዳደር ፍርድ ቤት በወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ፣ በክፍላተ ከተሞች ከፍተኛ ደረጃ፣ በከተማ ደረጃ ደግሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ቢኖሩ መልካም ነው ብሏል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ያለውን የመዋቅር ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...