Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ሙስና በመፈጸም የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ታሰሩ

  በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ሙስና በመፈጸም የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ታሰሩ

  ቀን:

  የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተርና ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር የነበሩትን ጨምሮ 11 ተጠርጣሪዎች፣ በመንግሥት ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡

  የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ዶ/ር ተክሌ ወልደ ገሪማ፣ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ መስፍን ኃይሉ፣ የማዕከሉ የሒሳብና ክፍያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገብረ ፃድቅ፣ የማዕከሉ ከፍተኛ ሲቪል መሐንዲስ አቶ ታምራት ኤርደሎ፣ አቶ ፍጹም ደጀኔ፣ ሰለሞን ላቀው ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ አቶ ደረጀ ጉደታ፣ የማዕከሉ ባልደረባና በሲቪል ሰርቪስ ተማሪ የሆኑት አቶ ባሻ ታከለ፣ በግል ሥራ ተሰማርተዋል የተባሉት ሃይማኖት ጥላሁን፣ ለይኩን ብርሃኑ፣ ፉፋ ሌንጂሳና ወርቅነህ መኮንን ናቸው፡፡ የተጠረጠሩበት የሙስና ጉዳይም ከጨረታ ሥራ ጋር የተገናኘ መሆኑን፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡

  ማዕከሉ በ2007 ዓ.ም. ከወርቅነህ ሥራ ተቋራጭ፣ ከፉፋ ሌንጂሳ ሥራ ተቋራጭና ከሌሎች ሥራ ተቋራጮች ጋር ውል ከፈጸመ በኋላ፣ ተጫራቾቹ ያሸነፉበት ዋጋ ስህተት ሳይኖረው፣ ተጠርጣሪዎቹ ሆን ብለው ስህተት እንዳለው በማስመሰልና በማረም፣ ገንዘቡን ከፍ አድርገው ላልተሠራ ሥራ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡

  ከውል ውጭ የክፍያ ሰነዶችን በማፅደቅ በኃላፊነት ማዕከሉን የመቆጣጠር ተግባራቸውን ወደ ጎን በማለት፣ ለሥራው በስፔስፊኬሽን የተቀመጠው ስካቫተርና ዶዘር ሆኖ እያለ በሎደር እንዲሠራ ማድረጋቸውንም መርማሪው ገልጿል፡፡ ተገቢ ቁጥጥር አለማድረጋቸውን፣ ከ32 ሔክታር የምንጣፍ ሥራ ውስጥ 21.3 ሔክታር ብቻ ተሠርቶ እያለ 30 ሔክታር እንደተሠራ አድርገው ማቅረባቸውንም መርማሪው ገልጿል፡፡ ከወርቅነህ መኮንን ሥራ ተቋራጭ ጋር ኮብልስቶን ለማንጠፍ በተገባው ውል ላይ የማይፈጸም ስፔስፊኬሽን በማውጣት ከውል ውጪ ሲሠራ አለመቆጣጠራቸውን መርማሪው አስረድቷል፡፡

  ተጠርጣሪዎቹ በተለይ የማዕከሉ ሠራተኞች የጨረታ ኮሚቴ ሆነው ሲሠሩ ጨረታዎቹ ሲፀድቁ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ሲገባቸው በዝምታ በማለፋቸው፣ በሌላ ሥራ ላይ የወጣ የጨረታ ሒደት በማስኬድ ላልተሠራ ሥራና ከውል ውጪ ክፍያዎች እንዲፈጸሙ ማድረጋቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ክፍያዎች በአጠቃላይ 20,592,534 ብር በመንግሥት ገንዘብ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በሙስና ተጠርጥረው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ታስረዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው የጠየቁ ቢሆንም፣ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ሥራዎች እንዳሉት ጠቅሶ ለሁለተኛ ጊዜ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ዓርብ ታኅሳስ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ፣ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበትን የገንዘብ መጠን የሚያሳየውን የኦዲት ሪፖርት ለታኅሳስ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ የዋስትና ጥያቄውን አልፎታል፡፡      

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...