Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበልማት ምክንያት የተፈናቀሉ 20 ሺሕ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም ዕቅድ ተያዘ

  በልማት ምክንያት የተፈናቀሉ 20 ሺሕ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም ዕቅድ ተያዘ

  ቀን:

  በተያዘው በጀት ዓመት በልማት ምክንያት ለዘመናት ከነበሩበት ቀዬ ተፈናቅለው ለችግር የተዳረጉ 20 ሺሕ አርሶ አደሮች፣ በድጋሚ እንደሚቋቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱራዛቅ ያሲን ሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በልማት ምክንያት የተነሱ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም አምስት ፕሮጀክቶች ተቀርፀዋል፡፡

  ‹‹በፕሮጀክቶቹ ላይ ከአርሶ አደሮቹ ጋር በቅርቡ ውይይት ይደረጋል፤›› ሲሉ አቶ አብዱራዛቅ ገልጸዋል፡፡

  ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አራት ቅርንጫፎች አሉት፡፡ እነሱም ቦሌ፣ የካ፣ አቃቂ ቃሊቲ ራሱን የቻለ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሚኖራቸው ሲሆን፣ እንዲሁም ንፋስ ስልክ ላፍቶና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች አንድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ይከፈትላቸዋል፡፡

  ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም የጊዜ ገደብ ቢኖረውም፣ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሰጠውን ኃላፊነት ይፈጽማል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡

  አቶ አብዱራዛቅ እንደገለጹት፣ በመጀመርያው ዙር 20 ሺሕ አርሶ አደሮችን የማቋቋም ዕቅድ ተይዟል፡፡ በቀጣይ ዓመታት ውስጥ ሌሎች ለችግር የተጋለጡ ተነሺ አርሶ አደሮች እንዲቋቋሙ የሚደረግ መሆኑን፣ ከዚህ በኋላ በልማት ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ አርሶ አደሮች የሚከናወነው ልማት አካል እንደሚሆኑ አቶ አብዱረዛቅ ተናግረዋል፡፡

  54 ሺሕ ሔክታር ስፋት ባላት አዲስ አበባ 30 ሺሕ ሔክታር መሀል ከተማ፣ ቀሪው ደግሞ የማስፋፊያ ቦታ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ የማስፋፊያ ቦታ በአጠቃላይ የአርሶ አደሮች ይዞታ ሲሆን፣ ቦታው ለተለያዩ ግንባታዎች በሚሰጥበት ወቅት ነባር አርሶ አደሮች ያለ በቂ ምትክ ቦታና ካሳ ሲፈናቀሉ ቆይተዋል፡፡

  መንግሥት ይህን ጉዳይ ዘግይቶም ቢሆን የተረዳው በመሆኑ፣ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው ለችግር የተዳረጉ አርሶ አደሮች በድጋሚ ለማቋቋም ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት መቋቋሙ ተገልጿል፡፡

  አቶ አብዱራዛቅ እንደሚናገሩት፣ በልማት ምክንያት የተነሱ አርሶ አደሮችን ቁጥር ለማወቅ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰበሰቡ ነው፡፡ በዚህ ዓመት 20 ሺሕ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም የታቀደ ሲሆን፣ በየዓመቱ የሚቋቋሙ አርሶ አደሮችን ቁጥር በ20 በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል፡፡

  ከዚህ በኋላ በልማት ምክንያት የሚነሱ አርሶ አደሮች ከመነሳታቸው ከሁለት ዓመት በፊት እንዲያውቁ ይደረጋል፡፡ የሚካሄደው ፕሮጀክትም አርሶ አደሮቹን በማካተት እንደሚሆንና ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮች እንደማይደገሙ አቶ አብዱራዛቅ ጠቁመዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...