Wednesday, August 10, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ40/60 ቤቶችን ሊረከብ ነው

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ40/60 ቤቶችን ሊረከብ ነው

  ቀን:

  – የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሙሉ በሙሉ ሊጠናቀቁ የተቃረቡ የ40/60 ቤቶችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተረክቦ ራሱ ዕጣ ለማውጣት እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በ40/60 ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉም ታውቋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የ40/60 ቤቶችን ዕጣ የሚያወጣው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶቹን ለማስረከብ እየተዘጋጀ መሆኑን፣ የባንኩ ኃላፊዎችም ቤቶቹን ለመረከብ ጉብኝትና ግምገማ እያካሄዱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  ለ40/60 ቤቶች በ2005 ዓ.ም. ምዝገባ ተካሂዶ ግንባታቸውም በዚያው ወቅት ቢጀመርም፣ በነበረው የኮንስትራክሽን ግንባታ ዋጋ ላይ ለውጥ በመምጣቱና የተለያዩ የዲዛይን ለውጦች በመደረጋቸው የዋጋ ክለሳ መካሄዱ ተገልጿል፡፡

  ባንኩ ተረክቦ በዕጣ ያስተላልፋል ተብሎ የሚጠበቀው በሰንጋ ተራና በክራውን ሳይቶች የተገነቡ 1,292 ቤቶችን ነው፡፡ በእነዚህ ቤቶች ላይ የሚጨመረው ዋጋ መጠን ግን አልተገለጸም፡፡

  ነገር ግን ለመጠናቀቅ የተቃረቡትና ለዕጣ ዝግጁ የሆኑት 1,292 ቤቶች ብቻ ሲሆኑ፣ ከ13 ሺሕ በላይ ተመዝጋቢዎች ሙሉ በሙሉ ክፍያ አጠናቀው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

  እነዚህ የ40/60 ቤቶች በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ቤቶቹ ለተጠቃሚዎች ባለመተላለፋቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡

  የ40/60 ቤቶች በሦስት ማዕቀፎች ተከፍለው ግንባታቸው እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የመጀመርያው ማዕቀፍ በክራውንና በሰንጋ ተራ ሳይቶች የተጀመሩት 1,292 ቤቶች ሲሆኑ፣ በ2005 ዓ.ም. ግንባታቸው ሲጀመር በ18 ወራት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ነበር፡፡ በሁለተኛው ማዕቀፍ የተጀመሩት 18,589 ቤቶች ደግሞ በስድስት ሳይቶች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ በሦስተኛው ማዕቀፍ ደግሞ 19,348 ቤቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ 39 ሺሕ ያህል የ40/60 ቤቶች በግንባታ ላይ ናቸው፡፡

  ይሁንና ግንባታቸው እጅግ ዘገምተኛ በመሆኑ ተመዝግበው እየተጠባበቁ በሚገኙ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ከመፍጠሩም በላይ፣ ማኅበራዊ ሕይወታቸውን እያናጋ መሆኑን የሚገልጹ ተመዝጋቢዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ለዚህም እንደ ምሳሌ የሚያነሱት ሙሉ ለሙሉ የከፈሉትም ሆነ በየወሩ የሚቆጥቡት ከግለሰቦች ላይ ለተከራዩዋቸው ቤቶች ወርኃዊ ክፍያ መገፍገፍ እንደሰለቻቸው ነው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የቅጥፈት እንጀራ!

  የዛሬው ጉዞ ከሲኤምሲ ወደ መገናኛ ነው። በዚህ በከባዱ የኑሮ...

  የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ድርድርና የአደራዳሪዎቹ ማንነት ያስከተለው ተስፋና ሥጋት

  በአክሊሉ ወንድአፈረው በብልፅግና የሚመራው በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መሀል ለሚደረገው ድርድር...

  ‹‹በድርቅ ምክንያት የሚቀርብልን የዕርዳታ ጥሪ ተበራክቷል›› አቶ አብዲሳ መሐመድ፣ በኦሮሚያ የኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሚቴ ሥራ አስኪያጅ

  ኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሚቴ (አይአርሲ) በኢትዮጵያ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ድንገተኛ...

  የመጻሕፍት ቡፌ

   ሕፃናትና ወጣቶች የትምህርት ዕረፍታቸውን ከትምህርት አጋዥ በተጨማሪ ልብ ወለድ፣...