Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር እንዲፈጠር ተጠየቀ

  የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር እንዲፈጠር ተጠየቀ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ የሕግ አማካሪና በአስተዳደሩ ሥር ያሉ ተቋማት ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ መክሰስና መከራከር ብቻ ሳይሆን፣ ቢሮው በሚሠራቸውም አላስፈላጊ ተግባራት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ተጠቆመ፡፡

  ቢሮው የ2009 በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ በየዘርፉ ላለው አመራር ባዘጋጀው የሁለት ቀናት (ጥቅምት 22 እና 23 ቀን 2009 ዓ.ም.) ግምገማዊ ሥልጠና ላይ በተገኙ የዘርፉ አመራሮች እንደተገለጸው፣ ማንኛቸውም በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈጠሩ ችግሮች ሲነሱ የፍትሕ ዘርፉ ተጠያቂ ነው፡፡ በመሆኑም ለሕግ የበላይነት ያገባኛል ብሎ መሥራቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ይኼንን ተግባር ለመፈጸም ግን ተጠያቂነት ያለበት አሠራር ሊዘረጋና የዘርፉ አመራር ችግር ፈጽሞ ሲገኝ ተግባራዊ ሊሆንበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

  የ2009 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድን በሚመለከት ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት የቢሮው የሥራ አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግሮች እንደነበሩ ኤክስፐርቱ ገልጸው፣ ቢሮው ተጠናክሮ እንዲሠራ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ምትኩ እንደገለጹት በዘርፉ አጠቃላይ የአቅም ማነስ፣ አገልግሎቱን በተገቢው ሁኔታ የመስጠትና የማስፈጸም ችግሮች እንዳሉ አምነዋል፡፡ ነገር ግን ቢሮው አሠራሩን እንደ አዲስ በማደራጀት ያሉበትን ችግሮች ለማስወገድ በትጋት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአስተዳደሩና በሕዝብ ጥቅም ላይ ችግሮች እንዳይመጡ ወይም እንዳይፈጠሩ ማድረግ ዋናው ሥራው መሆኑንም አክለዋል፡፡

  በመሬት አስተዳደር ጉዳይ ላይ ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱ ቢሆንም፣ ፍትሕ ቢሮው በቀጥታ ገብቶ ይኼ ይሁን ወይም አይደረግ የሚል ሥልጣን ስለሌለው፣ ከሚመለከታቸው የአስተዳደሩ አካልና ተቋማት አስተያየት እንዲሰጥ ሲጠየቅ ግን ተገቢ የሆነው የሕግ አስተያየት እንደሚሰጥ አቶ ዮሐንስ አስረድተዋል፡፡ የፍትሕ ቢሮው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን ለመዋጋት ያስችላል ያለውን ሰነድ ማዘጋጀቱንና ትክክለኛ የፍትሕ አሠራር ተግባራዊ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...