Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊአሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የወጣውን ክልከላ መንግሥት ተቃወመ

  አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የወጣውን ክልከላ መንግሥት ተቃወመ

  ቀን:

  አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ የሚከለክል መግለጫ መውጣቱን መንግሥት ተቃወመ፡፡

  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዝ እንዲታቀቡ ማሳሰቡን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃውመውታል፡፡

  አቶ ጌታቸው ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2008 ከአሜሪካ ድምፅ የእንግሊዝኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው የጉዞ ክልከላ የኢትዮጵያን ሁኔታ የማይገልጽ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

  ‹‹በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማበላሸት የሚሠሩ አሉ፤›› ሲሉ ተችተዋል፡፡ ለዚህም መንግሥት ማስረጃ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት አዘል ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ መሞታቸውን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸውንና ንብረቶች እየወደሙ መሆኑን ገልጾ አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዛ እንዲሰርዙ ያሳስባል፡፡

  በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የቆንስላ አገልግሎት ከአዲስ አበባ ውጪ መስጠት እንደማይችል ይጠቅሳል፡፡

  ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ወይም በመዘጋታቸው የአሜሪካ ኤምባሲ ከአሜሪካ ዜጐች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ላይ መገደቡን ይገልጻል፡፡

  አቶ ጌታቸው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ መግለጫው ኢትዮጵያን እንደማይገልጽና አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋች መሆኗን አስረድተዋል፡፡

  ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው የነበሩ ቱሪስቶች በአገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በርካቶች ጉዟቸውን እየሰረዙ መሆኑን አስጐብኚ ድርጅቶች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ከሞላ ጐደል 90 በመቶ የሚሆኑ ቀጠሮ የያዙ ቱሪስቶች እንደቀሩባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሦስት አስጐብኚዎች ተናግረዋል፡፡

  በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የፌዴራል ጠቅላይ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቱሪስቶችን የሚመለከት አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ማንኛውም ቱሪስት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መዘዋወር እንደሚችል ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡    

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...