Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትመሰለች መልካሙ ያመቱን ሁለተኛ የማራቶን ድሏን አጣጣመች

  መሰለች መልካሙ ያመቱን ሁለተኛ የማራቶን ድሏን አጣጣመች

  ቀን:

  – ሹሬ ደምሴ የቶሮንቶ ማራቶን ድሏን ደገመች

  በረዥም ርቀትና በአገር አቋራጭ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማ የሆነችው መሰለች መልካሙ ከአምና ወዲህ ባደረገቻቸው የማራቶን ሩጫ ውድድሮች ስኬታማ እየሆነች ነው፡፡ በጥር 2008 ዓ.ም. የዱባይ ማራቶን በ2፡22፡29 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ ስትወጣ፣ በዚያው ዓመት በሚያዝያ ወር በሀምቡርግ ማራቶን የቦታውን ሪከርድ 2፡21፡54 በሆነ ጊዜ በመስበር ድል መቀዳጀቷ ይታወሳል፡፡

  የዓመቱ ሦስተኛ ውድድሯ በሆነውና ባለፈው እሑድ (ጥቅምት 6 ቀን 2009 ዓ.ም.) በተካሄደው የአምስተርዳም ማራቶን፣ በ2፡23፡21 በመፈጸም አሸናፊ ሆናለች፡፡ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አበበች አፈወርቅ፣ መሰለችን ተከትላ ሁለተኛ ስትወጣ ባህሬናዊቷ አኒስ ቹምባ በሦስተኛነት ፈጽማለች፡፡ እ.ኤ.አ. የ2013 ለንደን ማራቶን ባለድሏና ፈጣኗ ሯጭ ጄፕቶና የ2012 አምስተርዳም ማራቶን ባለድሏ ኢትዮጵያዊቷ መሠረት ኃይሉ አራተኛና አምስተኛ ሆነው ፈጽመዋል፡፡

  በወንዶቹ ምድብ ኬንያዊው ዳንኤል ዋንጅሩ የቦታውን ሪከርድ በመስበር የራሱን ምርጥ ጊዜ 2፡05፡19 አስመዝግቧል፡፡ ኢንተርናሺናል አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር በድረ ገጹ እንደዘገበው፣ እስከ ስምንተኛ ድረስ ያለውን ቦታ ኬንያውያን ሲቆጣጠሩት ኢትዮጵያውያኑ ሙሉ ዋሲሁንና አበራ ኩማ ዘጠነኛና አሥረኛ ሆነዋል፡፡

  የ31 ዓመቷ መሰለች የማራቶን ምርጥ ሰዓትዋ ከአራት ዓመት በፊት በፍራንክፈርት ማራቶን ያስመዘገበችው 2፡21፡01 ነው፡፡ በ2001 ዓ.ም. በበርሊን በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና በ10 ሺሕ ሜትር ያገኘችው ብር ሜዳሊያ፣ በ2000 ዓ.ም. በቫሌንሺያ የቤት ውስጥ ሩጫ በ3000 ሜትር የተሸለመችበት ብር ሜዳሊያ፣ አዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር ወርቅ፣ በ2002 ዓ.ም. በናይሮቢ በ10 ሺ ሜትር ብር ሜዳሊያ ከስኬቶቿ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

  በተመሳሳይ ዜና ባለፈው እሑድ በካናዳ በተካሄደውና ከ25 ሺሕ በላይ በተካፈሉበት የቶሮንቶ ማራቶን የሴቶቹን ምድብ ኢትዮጵያዊቷ ሹሬ ደምሴ የአምና ድሏን ደግማለች፡፡ ዝናባማ በነበረው ውድድር የ20 ዓመቷ ሹሬ ያሸነፈችበት ጊዜ 2፡25፡16 ሲሆን፣ እሷን ተከትለው ሁለተኛና ሦስተኛ የወጡት ኢትዮጵያዊቷ ታደለች በቀለና ኬንያዊቷ ርብቃ ቼሰር ናቸው፡፡ በወንዶች ምድብ ኬንያዊው ፊልሞን ሮኖ በ2፡08፡26 ሲያሸንፍ፣ ኢትዮጵያዊው ሰቦቃ ዲባባ (2፡09፡46) እና ሌላው ኬንያዊ አልበርት ኮርየር ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...