Tuesday, August 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  በአዲስ ቢውልድ ዓውደ ርዕይ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፎ መጨመሩ ተጠቆመ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ዘጠና አንድ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶች የተሳተፉበት 7ኛው አዲስ ቢዩልድ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችና ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡ ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከጀርመን፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከግብፅ፣ ከቡልጋሪያና ከሌሎችም የዓለም ክፍሎች ከተውጣጡት የውጭ ድርጅቶች በተጨማሪ 20 የሚሆኑ የአገር ውስጥ ተቋማት የዓውደ ርዕዩ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

  በአገሪቱ በከፍተኛ ዕድገት ላይ በሚገኘው በዚህ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮሩ መሰል ፕሮግራሞች፣ ዘርፉን አንድ ዕርምጃ እንዲራመድ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡ ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ኢትኤል አድቨርታይዚንግ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሪት ሃይማኖት ተስፋዬ እንደምትለው፣ ዓውደ ርዕዩ ጥራት ያላቸውን የግንባታ ግብዓቶች የሚያመርቱ የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ባለቤቶች የሆኑ የውጭ ድርጅቶች ከአገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና ጥራት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶችን ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ማድረግና አገር ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያለመ ነው፡፡

  ከዚህ ቀደም በተደረጉ ተመሳሳይ ዓውደ ርዕዮች የውጭ አገር ተቋማት ተሳትፎ አነስተኛ እንደነበር የምትናገረው ወይዘሪት ሃይማኖት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ገልጻለች፡፡ ፕሮግራሙን እየጠበቁ ደጋግመው የሚሳተፉ ተቋማት ቁጥርም ጨምሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ተሳታፊ ከነበሩት ተቋማት መካከል አንዳንዶቹ በአገሪቱ ውስጥ መሥራት እንደጀመሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለአራት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ዛሬ የሚዘጋጀው የካይሮ ቴራፒ ሥልጠና የዝግጅቱ አካል ነው፡፡  

  የኮንስትራክሽን ዘርፍ በየዓመቱ በአማካይ በ12.43 በመቶ እያደገ ይገኛል፡፡ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻውም 5.3 በመቶ መድረሱን ከአራት ዓመታት በፊት የወጣ አንድ መረጃ ያሳያል፡፡ ዘርፉ በዚህ መጠን ዕድገት ቢያሳይም የተለያዩ ችግሮች እንዳሉበት ይነገራል፡፡ የኮንትራክተሮችና የአማካሪ ድርጅቶች አቅም ውስንነት፣ የዘመናዊ ቴክ ኖሎጂ እጥረትና የዲዛይን ችግር በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ 70 በመቶ የሚሆኑት ለኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚውሉ ግብዓቶች ከውጭ አገር እንደሚመጡና ይህም ሌላኛው ማነቆ በመሆኑ፣ ለዚህም ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ የግድ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኮንስትራክሽን ላይ ያተኮሩ ተመሳሳይ ፕሮግራሞችም የሚኖራቸው ፋይዳ የጐላ ነው ተብሏል፡፡  

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች