Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የክቡር ሚኒስትሩ ልጅ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከአባቷ ጋር እያወራች ነው]

  • ዳዲ፡፡
  • አቤት፡፡
  • ምንድን ነው ያወጣችሁት?
  • ምን አወጣን?
  • አሁን ጓደኞቼ ደውለው ጠይቂው ብለውኝ ነው፡፡
  • ምንድን ነው የምትጠይቂኝ?
  • ሰሞኑን ስላወጣችሁት አዋጅ?
  • እ… ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ?
  • ምንድን ነው ዳዲ?
  • ምኑ?
  • አዋጁ ነዋ፡፡
  • አንቺን እሱ አይመለከትሽም፡፡
  • ምንድን ነው የሚመለከተኝ?
  • እኔ አንቺ ላይ ያወጅኩት አዋጅ፡፡
  • የምን አዋጅ ነው ያወጅክብኝ?
  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፡፡
  • እና እሱ ምንድን ነው?
  • ከቤት መውጣት አትችይም!
  • ምን?
  • መጠጥ ቤት ማምሸት አትችይም!
  • ለምን?
  • እኔን ጥያቄ መጠየቅ አትችይም!
  • እሺ፡፡
  • እኔ ሳወራሽ ፊት ለፊት ማየት አትችይም!
  • እ…
  • መኝታ ቤትሽን በፈለግኩት ሰዓት መበርበር እችላለሁ!
  • እ…
  • ከመኝታ ቤትሽ የፈለኩትን ዕቃ መውሰድ እችላለሁ!
  • እ…
  • መኝታ ቤትሽ ውስጥ ያለውን ቲቪ እወስደዋለሁ!
  • እ…
  • ዲኤስቲቪና ዲሽ ማየት አትችይም!
  • እና ምን ልይ?
  • ኢቢሲ እሱንም በአንቴና፡፡
  • እሺ፡፡
  • የመኝታ ቤትሽን ኢንተርኔት አቋርጠዋለሁ!
  • እ…
  • ሞባይል ስልክሽን እቀማሻለሁ!
  • እ…
  • ሚኒስከርትና አጫጭር ቁምጣ ማድረግ አትችይም!
  • እ…
  • ጥፍር ቀለም መቀባት አትችይም!
  • እ…
  • ከቤት የምትወጪው ልማታዊ ስብሰባ ካለሽ ብቻ ነው!
  • እ…
  • ከጓደኞችሽ ጋር ተሰብስበሽ እኔን ማማት አትችይም!
  • እ…
  • ቀሪውን ዝርዝር ሳስታውሰው እነግርሻለሁ፡፡
  • ምን አድርጌ ነው ግን ዳዲ?
  • በጣም አስቸጋሪ ሆነሻል፡፡
  • ማንን አስቸገርኩ?
  • እኔን፣ እናትሽንና ወንድሞችሽን፡፡
  • ዳዲ እኔ ግን ልጅህ ነኝ፡፡
  • ቢሆንም አዋጅ አዋጅ ነው፡፡
  • እና ሁሉንም ነገር ተከልክያለሁ?
  • እንደዛ ማለት አይቻልም፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው የተፈቀደልኝ?

   

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቢሮ እየሄዱ ነው]

  • አንተ ቀስ በል እንጂ፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን ሆነሃል?
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ቀይ መብራት ነው እኮ የጣስከው?
  • ታዲያ ምን ችግር አለው?
  • እንዴት ችግር የለውም መብራት እየጣስክ?
  • ቸኩሉ ተብሏል አይደል እንዴ?
  • ማን ነው ያለው?
  • አዋጁ ነዋ፡፡
  • የትኛው አዋጅ?
  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፡፡
  • ምን?
  • ክቡር ሚኒስትር ምን ሆኑ?
  • አንተ ምን ሆንክ?
  • ዛሬ እንዴት ቁርስ እንደበላሁ ያውቃሉ?
  • እንዴት ነው የበላኸው?
  • በችኮላ፡፡
  • እ…
  • ያቺን ኪኒን የምታክል ዳቦ በትኩስ ሻይ አወራርጃት ምላሴ ራሱ አሯል፡፡
  • ሰውዬ ጤነኛ ነህ?
  • ክቡር ሚኒስትር ጊዜው የችኮላ ነው፡፡
  • ማን ነው ያለህ?
  • አስረድቶኛል በደንብ፡፡
  • ማን ነው ያስረዳህ?
  • ሁሌ የማመሽበት መጠጥ ቤት ነዋ፡፡
  • ማለት?
  • አንድ ሁሉን አዋቂ ጓደኛ አለኝ፡፡
  • እሺ፡፡
  • እንዲያውም ቅጽል ስሙ ጉግል ነው፡፡
  • ለምን?
  • በቃ ሁሉን ነገር ያውቃል፡፡
  • እሺ፡፡
  • እና ስለአዋጁ አስረድቶኛል፡፡
  • ምን ብሎ?
  • በቃ ሁሉን ነገር በአስቸኳይ ማስፈጸም መሆኑን ነዋ፡፡
  • እ…
  • እንዲያውም አሁን በአስቸኳይ ከመንጃ ፈቃድ ወደ ማስተርስ መገልበጥ አለብኝ፡፡
  • ምን አልክ?
  • ከዚች ኮንዶሚኒየም ቤት ወደ ቪላ በአስቸኳይ መግባት እንዳለብኝ ገብቶኛል፡፡
  • መቼም የማታመጣው ነገር የለም፡፡
  • ሚስቴንም በአስቸኳይ ውጭ ሄዳ እንድትወልድ ላስደርግ ነው፡፡
  • እ…
  • እንዲያውም የልጄን ስም ራሱ…
  • እ…
  • አስቸኳይ ብየዋለሁ፡፡
  • አንተ?
  • ክቡር ሚኒስትር መቼም እናንተም በአስቸኳይ ትለውጡታላችሁ አይደል?
  • ምኑን?
  • ዴሞክራሲውን!

  [ክቡር ሚኒስትሩ አንድ ሚኒስትር ጋ ደወሉ]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የጀርመኗ ቻንስለር ትመጣለች አይደል?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ላገኛት እፈልጋለሁ፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምነው?
  • ጉብኝቷ ከእርስዎ መሥሪያ ቤት ጋር አይገናኝም፡፡
  • የንግድ ልዑክ አይመጣም እንዴ?
  • ኧረ የቻንስለሯ የጽሕፈት ቤት ሰዎች ናቸው የሚመጡት፡፡
  • እንዴት የንግድ ልዑክ አይመጣም?
  • እነርሱም እኮ ከእርስዎ መሥሪያ ቤት ጋር አይገናኙም፡፡
  • በግሌ ነው የፈለግኳቸው፡፡
  • ለምን?
  • ጀርመኖች እኮ አሪፍ ዕቃ ነው ያላቸው፡፡
  • ማለት?
  • አሪፍ አሪፍ ዕቃ ነዋ ያላቸው፡፡
  • እና ቢኖራቸውስ?
  • ከቻይና ዕቃ ይሻላል ብዬ ነዋ፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር አደብ ይግዙ፡፡
  • ምን አደረግኩ?
  • በአደባባይ አደረጉት፡፡
  • ምኑን?
  • ኪራይ ሰብሳቢነቱን፡፡
  • ዕቃ ላስመጣ እኮ አይደለም፡፡
  • እና ምን ሊያደርጉ ነው?
  • ዕቃ አስመጪዎችን ከዕቃ አምራቾች ጋር ላገናኝ፡፡
  • ሊደልሉ?
  • ድለላ ሳይሆን የኮሚሽን ሥራ ነው፡፡
  • ምን?
  • የኮሚሽን ሥራ፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር ይህን አሳፋሪ ተግባር ያቁሙ፡፡
  • ስማ ሥራዬን ከማንም በላይ ነው የምሠራው?
  • ማለት?
  • ኮሚሽን ከፍላችሁት ራሱ የሚሠራላችሁ ሰው የታለ?
  • እውነት ብሶብዎታል፡፡
  • ለማንኛውም የመጣ ቢመጣ አላቆምም፡፡
  • ምኑን?
  • የኮሚሽን ሥራዬን!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊያቸውን አስጠሯት]

  • ትናንት በጊዜ ለምን ወጣሽ?
  • ፈርቼ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምንድን ነው የፈራሽው?
  • ትራንስፖርት የለም ሲሉ ሰምቼ፡፡
  • ለምንድን ነው የሌለው?
  • ያው በጊዜያዊው ግርግር ነዋ፡፡
  • ሥራ ግን እንዳትበድዪ፡፡
  • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለመሆኑ ቀጠሮ አለኝ?
  • ኧረ ምንም የለዎትም፡፡
  • ቀኑን ሙሉ?
  • ከሰዓት አለዎት፡፡
  • ጠዋትስ?
  • ከአማካሪዎ ጋር ስለሚወያዩ አስታውሺኝ ብለውኝ ነበር፡፡
  • በቃ ጥሪው፡፡

  [አማካሪያቸው ቢሮ ገባ]

  • አንተ!

  [ዝም]

  • ስማ እንጂ፡፡

  [ዝም]

  • እያናገርኩህ እኮ ነው?

  [ዝም]

  • አንተን አይደል እንዴ?
  • ለምን አይተውኝም ክቡር ሚኒስትር?
  • በጣም ነው የተናናቅነው፡፡

  [ዝም]

  • አንተ ሰውዬ፡፡

  [ዝም]

  • እኔ ጠፋሁ፡፡

  [ዝም]

  • አውራ፡፡
  • አውራ ፓርቲው ምን ሆነ?
  • ማን ስለእሱ ጠየቀህ?
  • ስለምኑ ነው የጠየቁኝ ታዲያ?
  • ለምንድን ነው የማታወራው?
  • ፈርቼ፡፡
  • ምኑን?
  • አዋጁን፡፡
  • ለምን ፈራኸው?

  [ዝም]

  • አንተን እኮ ነው፡፡

  [ዝም]

  • መልስልኝ እንጂ?
  • ምላሼ አንድ ነው?
  • ምንድን ነው ምላሽህ?
  • ዝምታ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...

  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተጀመረው የድርድር ሒደት አሳታፊ እንዲሆን ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወዳጃቸው ከሆነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር ሻይ ቡና እያሉ በኬንያ ስለተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተጫወቱ ነው]

  ኬንያ በዚህ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም ነበር ክቡር ሚኒስትር። አዎ። ጥሩ ዝግጅት አድርገውበታል። ቢሆንም... ቢሆንም ምን ክቡር ሚኒስትር?  እባክህ ክቡር ሚኒስትር የምትለውን ነገር አቁም። ወዳጅ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...