በየዓመቱ የመስከረም የመጨረሻ እሑድ በቡራዩ ገፈርሳ የሚከበረው የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል ተራዘመ፡፡
‹‹ከክረምቱ ወራት ወደ በጋው የብርሃን ወቅት እንኳን በሰላም አሸጋገርከን›› በማለት የምስጋናና የመልካም ምኞት ምርቃት የሚካሄድበት የገፈርሳው የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል ሁልጊዜ የሚውለው ከቢሾፍቱው የኢሬቻ በዓል በኋላ ነው፡፡
የዘንድሮው በዓል መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚውል ቢሆንም፣ በቢሾፍቱ በደረሰው አደጋ ‹‹ሐዘን ላይ ነን›› በሚል የአካባቢው ሽማግሌ ‹‹አባ መልካ›› በዓሉ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጸዋል፡፡
የመልካ አቴቴ ኢሬቻ አባ ገዳዎች፣ የአገሪቱ ሽማግሌዎችና በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ታዳሚዎች የሚገኙበት በዓል ነው፡፡