Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር እየሄዱ ነው]

  • ምንድን ነው አንተ?
  • ሠልፍ ነው እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን?
  • አያዩትም እንዴ?
  • የምን ሠልፍ ነው?
  • የመኪኖቹን ሠልፍ ይመልከቱት እስቲ፡፡
  • ሠልፍ ተከልክሏል አይደል እንዴ?
  • አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምንድን ነው?
  • በቃ ሠልፍ ይፈራሉ አይደል?
  • ለምን አልፈራ?
  • እሱኛውን ሠልፍ አይደለም እኔ የምልዎት፡፡
  • ታዲያ የምን ሠልፍ ነው?
  • ዛሬ መስቀል አደባባይ በዓል አለ፡፡
  • የምን በዓል?
  • የደመራ በዓል፡፡
  • እና?
  • በቃ ለበዓሉ ዝግጅት ስለሚደረግ ነው፡፡
  • የምን ዝግጅት ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ለበዓሉ እኮ በርካታ ሰው መስቀል አደባባይ ይወጣል፡፡
  • ሠልፍ ነው የሚወጣው?
  • በዓሉን ለማክበር ነው የሚወጣው፡፡
  • ለመሆኑ በዓሉን መንግሥት ያውቀዋል?
  • ክቡር ሚኒስትር በዓሉ እኮ ሃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡
  • ቢሆንስ?
  • ሁሌም የሚከበር ነዋ፡፡
  • አሁን ጥያቄው ሕዝቡ ለመሰብሰብ አስፈቅዷል ወይ?
  • እርስዎ ስለደመራ በዓል አያውቁም እንዴ?
  • እ…
  • በዩኔስኮ የተመዘገበ ምናምን እያሉ ያወራሉ አይደል እንዴ?
  • በዩኔስኮ ቢመዘገብስ?
  • እኮ ትልቅ ሃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡
  • ለመሆኑ ምንድን ነው የሚደረገው?
  • ከየቤተ ክርስቲያኑ መዘምራን መጥተው ይዘምራሉ፡፡
  • እሺ፡፡
  • ከዚያም በኋላ እሳት ይቀጣጠላል፡፡
  • እሳት?
  • አዎን፣ ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • በአስቸኳይ መቆም አለበት፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • እስር ቤቱ ሲቃጠል፣ መንግሥት ነው ተባለ፡፡
  • እሱማ ተብሏል፡፡
  • ገበያውም ሲቃጠል ሆን ብላችሁ ነው ተባለ፡፡
  • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እና አሁንም እናንተ ናችሁ ብንባልስ?
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼ እኮ በየዓመቱ የሚደረግ በዓል ስለሆነ ችግር የለውም፡፡
  • ለመሆኑ ለምንድን ነው የሚቃጠለው?
  • በቃ ደመራው ከተደመረ በኋላ የሚወድቅበት አቅጣጫ ትርጉም አለው፡፡
  • ማለት?
  • በደቡብ ወይ በሰሜን ወይ በምሥራቅ ወይ በምዕራብ ሲወድቅ ትርጉም አለው፡፡
  • ምን?
  • ብቻ ለዘንድሮ ደመራ መፀለይ አለብን፡፡
  • ምን ብለን?
  • አወዳደቁ ይመር!

   

  [ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ዳያስፖራ ደወለላቸው]

  • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት ነህ?
  • ምነው በአሁኑ ኒውዮርክ ቀሩ?
  • ሥራ በዝቶብኝ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በየዓመቱ ኒውዮርክ አይቀሩም ነበር እኮ?
  • አገሪቷ ውስጥ ያለውን ነገር እያወቅከው?
  • ለነገሩ ብዙ የራስ ምታት አለብዎት፡፡
  • የራስ ምታት ብቻ?
  • ግን ምን እየሆናችሁ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን ሆንን?
  • ደግሞ ሶሻል ሚዲያ ልትከለክሉ ነው?
  • ምን እያወራህ ነው?
  • ይኸው መንግሥት ስለሶሻል ሚዲያ ችግር ኒውዮርክ ውስጥ አወራ አይደል እንዴ?
  • ስማ ይኼ ሶሻል ሚዲያ የሚሉት ቡድን አደገኛ ነው፡፡
  • ሶሻል ሚዲያ እኮ ቡድን አይደለም፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው?
  • ፌስቡክ ያውቃሉ?
  • ልጆቼ ሲጠቀሙ አያለሁ፡፡
  • ትዊተርንስ ያውቁታል?
  • ሲወራ ሰምቻለሁ፡፡
  • በቃ ይኼውልዎት ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም፣ ስናፕ ቻትና ሌሎችም ፕላትፎርሞች ናቸው ሶሻል ሚዲያ የሚባሉት፡፡
  • ስማ እኔ ያልካቸውን አላውቃቸውም፤ ማወቅም አልፈልግም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ችግራችሁ እኮ ይኼ ነው፡፡
  • ምንድን ነው ችግራችን?
  • በቃ የሕዝቡን ችግር አታውቁትም፣ ማወቅም አትፈልጉም፡፡
  • ስማ እና በሶሻል ሚዲያ አገሪቷ ትፈራርስ?
  • አገሪቷ በሶሻል ሚዲያ ነው እንዴ የተገነባችው?
  • እ…
  • ብቻ እኔ መበስበሳችሁን ነው የተረዳሁት፡፡
  • በል በል መስመር አትለፍ፡፡
  • የምን መስመር?
  • ለአገሪቷ የሚያስፈልጋት ሶሻል ሚዲያ አይደለም፡፡
  • እና ምንድን ነው የሚያስፈልጋት?
  • ሶሻል ላይፍ!

  [አንድ ደላላ ለክቡር ሚኒስትሩ ደወለላቸው]

  • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ፈልገህ ነው?
  • የሚገርም ሥራ አግኝቻለሁ ክቡር ሚኒስትር?
  • የምን ሥራ ነው?
  • አንድ ትልቅ ኢንቨስተር ሊያገኝዎት ይፈልጋል፡፡
  • የምን ኢንቨስተር ነው?
  • ትልቅ ሀብት ኢንቨስት ለማድረግ ይፈልጋል፡፡
  • ስማ እኔ ከ100 በላይ ካልሆነ ማናገር አቁሜያለሁ፡፡
  • ማለት?
  • ከ100 ሚሊዮን መብለጥ አለበት፡፡
  • መቶ ሚሊዮን ብር?
  • መቶ ሚሊዮን ዶላር ነው እንጂ፡፡
  • አይ ክቡር ሚኒስትር ለነገሩ ይኼ ሦስት መቶ ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ኢንቨስት ማድረግ ይፈልጋል፡፡
  • እንደዚያ ከሆነ እንኳን ጥሩ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ስጦታ ይዞ ነው የመጣው፡፡
  • ችግሩ እኮ አሁን ወቅቱ ጥሩ አይደለም፡፡
  • እንዴት?
  • ሰሞኑን ነዋ ተገምግሜ ሒሴን የዋጥኩት፡፡
  • ታዲያ ሒስዎትን ማወራረድ አለብዎታ፡፡
  • በምን?
  • በኮሚሽን!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • እንዴት ነበር ክቡር ሚኒስትር?
  • ምኑ?
  • ግምገማው፡፡
  • ጥልቅ ግምገማ ነው ያካሄድነው፡፡
  • እውነት?
  • አዎን ተሃድሷችንም ጥልቅ ነው የሚሆነው፡፡
  • እና ግምገማው ወሳኝ ነበር ነው የሚሉኝ?
  • ስማ እኔ ራሴ ብዙ ነገር ነው የተማርኩበት፡፡
  • ምን ተማሩ?
  • የጀመርኩትን ሕንፃ ራሱ ላፈርሰው ነው፡፡
  • ለምን?
  • መሠረቱን በጥልቅ መቆፈር እንዳለብኝ ስለተረዳሁ፡፡
  • ምን?
  • በቃ ሰው ይኼን ያህል ፎቅ እያለ በየጊዜው ከምገመገም…
  • እ…
  • ሕንፃዬን ወደታች ሠርቼ ባከራየው ሰው አፍ ውስጥም አልገባም፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • ከዚህም ባለፈ የንግድ ዓለም ውስጥ ራሱ በጥልቀት ልገባ ነው፡፡
  • ይኼ ነው በጥልቀት መታደስ?
  • ብዙ ነገር ተማርኩበት አልኩህ እኮ፡፡
  • የሕዝቡ ጥያቄስ?
  • የሕዝቡ ጥያቄ ተመለሰ አይደል እንዴ?
  • በምን?
  • በቴክስት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ሚስታቸው ጋ ደወሉ]

  • አቤት፡፡
  • ያ ሕንፃ በአስቸኳይ ይፍረስ፡፡
  • የትኛው ሕንፃ?
  • እዚያ መሀል ከተማ የጀመርነው፡፡
  • ምን እያወራህ ነው ሰውዬ?
  • ይፍረስ አልኩሽ እኮ፡፡
  • ለመሠረት ስንት ገንዘብ እንዳፈሰስንበት እያወቅክ?
  • እኮ መሠረቱ ድጋሚ መቆፈር አለበት፡፡
  • ለምን?
  • በጥልቀት መሠረቱን ገንብተን ከላይ ትንሽ ፎቅ ማድረግ አለብን፡፡
  • እኮ ለምን?
  • ዓይን ውስጥ መግባት አያስፈልገም፡፡
  • እና ምን ልናደርግ?
  • በቃ ወደታች ብዙ ፎቅ ገንብተን ማከራየት ነው፡፡
  • ተገምግመህ አይደል እንዴ የምትወጣው?
  • ከግምገማው የተማርኩት ዘዴ ነው፡፡
  • ማለት?
  • ቢዝነስ ውስጥ ራሱ በጥልቀት መግባት እንዳለብኝ ተረድቻለሁ፡፡
  • ሥራህስ?
  • የቱ ሥራ?
  • የሚኒስትርነቱ?
  • በቃ የቀድሞ ባለሥልጣናት ሊመለሱ ነው፡፡
  • የትኞቹ ባለሥልጣናት?
  • በፊት ለቀው የሄዱት፡፡
  • በመተካካት ስትራቴጂ የተለወጡት?
  • አዎና፡፡
  • ለሕዝቡ መተካካት የሚለውን ስትራቴጂ ምን አደረግነው ልትሉት ነው?
  • ቀየርነው እንላቸዋለና፡፡
  • በምን?
  • በመመላለስ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...

  አዲስ አበባ እንዳይገቡ በተከለከሉ ዜጎች ጉዳይ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተወያይተው ችግሩ እንዲፈታ አደረጉ

  ለሳምንታት በርካታ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረውና ከአማራ ክልል በደብረ ብርሃን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...