Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት ዋስትና የተከለከሉት ጭብጥ በሌለው ክስ መሆኑን ለፍርድ ቤት አስረዱ

  የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት ዋስትና የተከለከሉት ጭብጥ በሌለው ክስ መሆኑን ለፍርድ ቤት አስረዱ

  ቀን:

  ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ ጋር ተጠርጥረው ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ክስ ነፃ ሆነው በግብር ጉዳይ ተከላከሉ የተባሉት የኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ተከልክለው በእስር ላይ የሚገኙት ጭብጥ በሌለው ክስ መሆኑን ለፍርድ ቤት አስረዱ፡፡

  ጂኤች ስሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ስማቸው፣ መስከረም 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት በጽሕፈት ቤት ቀርበው ከጠበቆቻቸው ቀጥለው አቤቱታቸውን አሰምተዋል፡፡

  አቶ ስማቸው እንደተናገሩት በድርጅታቸውና በራሳቸው ላይ የቀረበው የግብር ክስ፣ ለኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ማስፋፊያ ፕሮጀክት የወሰዱትን የባንክ ብድር ወለድ በሥራ ላይ ባለው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ላይ አወራርደዋል የሚል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  እንደ ዓቃቤ ሕግ ክስ ከሆነ ወለዱ መወራረድ ያለበት የማስፋፊያ ሥራው ሲያልቅ እንጂ በሥራ ላይ እያለ ማወራረድ እንደሌለባቸው የሚገልጽ መሆኑን የተናገሩት አቶ ስማቸው፣ ዓቃቤ ሕግ በአንድ በኩል መወራረዱን እያመነ በሌላ በኩል ቀድሞ መወራረዱን እንደ ወንጀል ቆጥሮ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

  ዓቃቤ ሕግ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ወለዱ መወራረዱን የገለጸ ቢሆንም፣ በተጠቀሱት ዓመታት ዓቃቤ ሕግ ተጀምሯል ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት አለመጀመሩንና ምንም ዓይነት ብድርም አለመውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ከተከፈተ ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ የራሱን ብድር እያወራረደ ያለውን ወለድ፣ የማስፋፊያው ፕሮጀክት አድርጎ ማቅረቡ ከእውነት የራቀ ክስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም ምስክሮች እንዳሉት ለፍርድ ቤቱ ካስመዘገበ በኋላ ሳያሰማ ያቋረጠው ክሱ ምንም ጭብጥ እንደሌለው በማወቁ ስለሆነ፣ ምንም ጭብጥ በሌለው ክስ በእስር መቆየታቸው ተገቢ አለመሆኑን፣ ዓለም አቀፍም ሆነ አገር አቀፍ የሕግ ድንጋጌዎችን የሚጥስ እንደሆነ በማስረዳት ዋስትናቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

  የዋስትና ጥያቄ ከመብትም ባለፈ ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን በመጠቆም ስለደንበኛቸው የተከራከሩት ጠበቃቸው አቶ ታምሩ ወንድማገኘሁ፣ የዋስትና ጥያቄ በ48 ሰዓታት ውስጥ ውሳኔ መሰጠት እንዳለበት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 66 መደንገጉን አስታውሰዋል፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67 ሥር የማይወድቅ ጉዳይ በመሆኑ መልስ መሰጠትም እንደሌለበት አቶ ታምሩ አስረድተዋል፡፡ በሕገ መንገሥቱ አንቀጽ 13 እና 25 መሠረትም ዋስትና መከበር እንዳለበት ሌላኛው የአቶ ስማቸው ጠበቃ አቶ ለምለም ሲሳይ ተናግረው፣ በዕለቱ ከእስር እንዲለቀቁም ጠይቀዋል፡፡

  ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ ዓቃቤ ሕግ ዋስትና እንዳይሰጥ ተቃውሞ ያቀረበበት መነሻ ምክንያት ከክሱ የመነጨ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የማስተናገድ ኃላፊነት አለበት ብሏል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ የሚያቀርበው መቃወሚያ የተጠየቀውን የዋስትና መብት የሚያስከለክል መሆን አለመሆኑን መርምሮ ብይን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

  ከአቶ ስማቸው ከበደ ጋር የዋስትና ጥያቄ አቅርበው የነበሩት የአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ሲሆኑ፣ በእሳቸው ላይ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ አለማቅረቡን ገልጸው ጉዳያቸው ተነጥሎ እንዲያይላቸው አመልክተው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን የሁለቱንም ተከሳሾች ጉዳይ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

  ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ የአገሪቱ...

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...