Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዝንቅየእንቁጣጣሽ ዋዜማ የገበያ ድባብ

  የእንቁጣጣሽ ዋዜማ የገበያ ድባብ

  ቀን:

  ፍቅርና ሞት

  እንነሳ ይሆን፤ እኛም ከንቅልፋችን፤ ሁሉን ነገር ረስተን፡፡

  እጅህ ውስጥ ያለችው ኧረ ነፍሴስ ብትሆን

  ምንም አታስታውስ፤ ነፋስ እንዳሸዋ

  ዘምባባውን ረስቶ ወደ ሚሸሹበት ረጃጅሞችና ሰማያዊ ጥላ

  ወጨፎ ሲጠርገው የጨላለመውን ያንን ምድረበዳ?

  አሁን እንደፊት ታስታውስ ይሆን፤ ምንም እንኳን ቢያልፉ

  አንድ ሺ ጠፈሮች፤ፕላኔቶችንም እዚያ ሲያናፍሱ

  ያን ባዶ ሕዋህው በጎረና ልሳን?

  የነፍሴ ነፍስ ሆይ፤ ፈጽሞ አይረሳም አንዲት ቃልም ብትሆን፤

  ፍቅሬ ወለላዬ፤ አንጋፈጠውም ለየብቻችን

  የጠፉት ፀሐዮች ምድረበዳውን፡፡

  የምትዞርበት የኛለም ብትሆንም ሕዋህውን ጭምር ከቶ አንፈራውም፤

  አብረን እንሄዳለን አንለያይም

  ለየብቻ ሆነን አንጋፈጠውም ያንን ዘላለም፡፡

  • ከሳራ ቲስዴል (1884 – 1930)

  ስድ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ (1925 – 2007)

  *******

  የዕድሜ ባለፀጎች መንደር

  አኪያሮቢ በተሰኘች የጣልያን መንደር ከመቶ የሚያልፉ የዕድሜ ባለፀጎች ስለሚበዙ እዚህ መንደር የሰዎችን ዕድሜ የሚያረዝመው ምንድነው? በማለት ሳይንቲስቶች ለስድስት ወራት ምርምር አደረጉ፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ ተፈጥሯዊ ምግብ፣ ወሲብ ወይስ ሌላ ነገር? ሲል ጥናቱ ይጠይቃል፡፡ ነዋሪዎች የዕድሜ ባለፀጎች በመሆናቸው የደቡብ ምዕራብ ጣልያን መንደሯ አኪያሮሊ እንደማንኛውም ቦታ አይደለችም፡፡ የ100 ዓመት አዛውንቱ አንቶኒዮ ቫዛሎና የ93 ዓመቷ ባለቤታቸው አሚና በጥናቱ ከተካተቱ ነዋሪዎች መካከል ናቸው፡፡ በዚህች መንደር 700 የሚሆኑ ነዋሪዎች አሉ፡፡ ከአሥር ነዋሪ አንዱ ዕድሜው ከ100 በላይ ነው፡፡ የሮም ሳፒዛኒ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የደረሱበት ውጤት እንደሚያሳየው የመንደሯ የዕድሜ ባለፀጎች ከተለመደው ውጭ የደም ዝውውራቸው ጥሩ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ የሆርሞን ጉዳይ ነው፡፡ የነዋሪዎቹ የሆርሞን መጠን የተስተካከለ በመሆኑ ምንም ዓይነት የደም ዝውውር ችግር የለባቸውም፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው የመንደሯ ነዋሪዎች የሚመገቡት ተፈጥሯዊ ምግብ መሆንና አዘውትረው እንቅስቃሴ የሚያደርጉ መሆናቸው እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

  ***********

  ከሚስታቸው ለመሸሽ ሲሉ ራሳቸውብ ለእስር የዳረጉት ሰው

        አሜሪካ ካንሳስ ውስጥ ጆን ሪፕል የተባሉ የ70 ዓመት አዛውንት ከሚስታቸው መጨቃጨቃቸውን ተከትሎ ሽጉጣቸውን  ይዘው በአቅራቢያ ወደገሚኝ ባንክ ሄደው ወደ አንዱ መስኮት ጠጋ ይሉና ለባንኩን ሠራተኛ ብር እንደሚፈልጉ የጻፉበትን ወረቀት ይሰጣሉ፡፡ ከዚያም 3,000 ዶላር ይቀበላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን እንደ ዘራፊ ቀማኛ በቶሎ ተሯሩጠው ከባንኩ በመውጣት ለማምለጥ አልሞከሩም፡፡ ይልቁንም ለባለጉዳዮች ማረፊያ ይሆኑ ዘንድ ወደ ተደረደሩት ሶፋዎች ጠጋ ብለው ኮራ ብለው ቁጭ ይላሉ፡፡ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛም ወዲያው መጥቶ አፈፍ አድርጎ እንደያዛቸውና ከዚያም ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደተወሰዱ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በመጨረሻ ገንዘቡ ለባንኩ የተመለሰ ሲሆን፣ አዛውንቱ ከቤት ሲወጡ ከእሷ ጋር ከመጨቃጨቅ ወህኒ መውረድ እንደሚመርጡ ለሚስታቸው መናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

  *******

  የቻይናን ታላቁ ግንብ ለመታደግ ቻይናውያን እየተረባረቡ ነው

  የቻይና ታላቁ ግንብ (ግሬት ዋል) አገሪቷ ከምትኮራባቸው ሀብቶች አንዱና ዋነኛው ሲሆን፣ የአገሪቱ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ለግንቡ እድሳት እንደሚያስፈልግ ያሳወቀው በቅርቡ ነበር፡፡ ከ2,000 ዓመታት በፊት መገንባቱ የሚነገርለት ግንቡ እየፈራረሰ በመሆኑ የአገሪቱ ዜጎች የገንዘብ ዕርዳታ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል፡፡ ጥሪው ከቀረበበት ዕለት አንስቶ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ 16,000 የሚሆኑ ሰዎች ገንዘብ ለግሰው ወደ 45,000 ዶላር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ 1.7 ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብ ዕቅድ ያለው የአገሪቱ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን አሁንም የሕዝቡን ድጋፍ እየጠየቀ ነው፡፡ ብዙዎች ግንቡን ለመታደግ ገንዘብ ለመስጠት ፍቃደኛ ቢሆኑም አንዳንዶች ያለ ሕዝብ መዋጮ መታደስ ይችላል በሚል ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...