Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊግንባታቸው የተጠናቀቁ 1,292 የ40/60 ቤቶችን ለማስተላለፍ የካቢኔ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ

  ግንባታቸው የተጠናቀቁ 1,292 የ40/60 ቤቶችን ለማስተላለፍ የካቢኔ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ

  ቀን:

  • 34,605 ተመዝጋቢዎች ከ40 እስከ 100 ፐርሰንት ቆጥበዋል

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም በሰንጋ ተራና በአቃቂ ቃሊቲ ክራውን ሆቴልን አለፍ ብሎ ያስገነባቸው 1,292 (19 ብሎኮች) ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ በዕጣ ለማከፋፈል፣ የአስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡

  የቤቶቹ ፕሮግራም ይፋ በተደረገበት በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ድረስ 147,765 ሺሕ ቤት ፈላጊዎች ሲመዘገቡ፣ ቤቶቹም ባለ አንድ፣ ባለሁለትና ባለሦስት መኝታ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

  በምዝገባ ፕሮግራሙ እንደተገለጸው ማንኛውም ተመዝጋቢ ቤቶቹን ለማግኘት 40 በመቶ የሚሆነውን የቤቱን ዋጋ በየወሩ ቆጥቦ ማጠራቀም ግዴታው እንደሆነ የተቀመጠ ሲሆን፣ መቶ በመቶ ሙሉ ክፍያውን መፈጸም ደግሞ ቅድሚያ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጾ ነበር፡፡

  ለቤቶቹ ሙሉ ክፍያ በወቅቱ የተገለጸ የገንዘብ መጠን ቢኖርም፣ 14,366 ተመዝጋቢዎች ግን የቤቶቹ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል ግምት በመውሰድ ከ100 ፐርሰንት በላይ መቆጠባቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከ40 በመቶ እስከ 100 ፐርሰንት የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች 34,605 መሆናቸውም ታውቋል፡፡

  በተለይ ሙሉ በሙሉ የቤቶቹን ክፍያ ቀደም ሲል የፈጸሙ ተመዝጋቢዎች በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ነበር፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተገባላቸው ቃል መሠረት ቤቶቹ ተገንብተው ባለመረከባቸው መንግሥት በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸውም ሲጠይቁ ነበር፡፡ ከመኖሪያ ቤት ችግር አንፃር ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ክፍያ መፈጸማቸው የመንግሥትን ቃል አምነው እንደነበር የሚናገሩት ተመዝጋቢዎቹ፣ ገንዘቡን ቢሠሩበት ኖሮ ከፍተኛ ጥቅም ያገኙበት እንደነበር በቁጭት ይናገራሉ፡፡

  የ40/60 ኮንዶሚኒየም ቤቶች በስምንት ሳይቶች ማለትም በሰንጋ ተራ፣ በክራውን ሆቴል አካባቢ፣ በቦሌ ቡልቡላ፣ በአስኮ (እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ)፣ በገርጂ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል አካባቢ፣ በመገናኛ፣ በመሪና በቦሌ አያት 14,273 ቤቶች እየተገነቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

  በሁለቱ ሳይቶች ሰንጋ ተራና ክራውን ሆቴል አካባቢ 19 ብሎኮች ማለትም 1,292 ቤቶች በሚያዝያ ወር 2007 ዓ.ም. እንደሚተላለፉ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ባልታወቀ ምክንያት ሳይተላለፉ ዓመት አልፎታል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...