Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የግል ባንኮችና የፍላጎቱን ያህል ያላደገው የብድር አቅርቦት

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ባንኮች ለተበዳሪዎቻቸው የሚሰጡት የብድር መጠን ከፍላጎቱ ጋር ባይጣጣም፣ የሚያበድሩት የብድር መጠን ከዓመት ዓመት እያደገ መጥቷል፡፡ የተቀማጭ ገንዘባቸውን መጠንም እንዲሁ በየጊዜው ማሳደግ ችለዋል፡፡

  ይሁን እንጂ የግል ባንኮች ከሚቀርብላቸው የብድር ፍላጎት አንፃር የሰጡት ብድር አነስተኛ ስለመሆኑ ያነጋገርናቸው የባንክ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ በ2008 በጀት ዓመት የግል ባንኮች ብድር መጠንን ተንተርሶ አስተያየታቸውን ከሰጡን የባንክ ባለሙያዎች መገንዘብ እንደተቻለው፣ የብድር ፍላጎቱን ማሟላት ባይቻልም ባንኮች እየሰጡ ያሉት ብድር በማደግ ላይ ይገኛል፡፡

  በ2008 በጀት ዓመት የ16ቱ የግል ባንኮች የብድር ክምችት መጠን 92 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን፣ ይህ ብድር መጠን ከቀደመው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ12 በመቶ በላይ ጭማሪ አለው ተብሏል፡፡ ከ16ቱ ባንኮች ከፍተኛ ብድር ያቀረቡት አዋሽና ዳሸን ባንኮች ናቸው፡፡

  አዋሽ ባንክ ያቀረበው የብድር መጠን 15.4 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ዳሸን ደግሞ 12.7 ቢሊዮን ብር ማበደር ችሏል፡፡ ከሁለቱ ባንኮች ቀጥሎ ከፍተኛ መጠን ያለውን ብድር የሰጠው ሕብረት ባንክ ሲሆን፣ በዓመቱ በጠቅላላው 8.5 ቢሊዮን ብር አበድሯል፡፡ 

  ይሁን እንጂ በበጀት ዓመቱ ለብድር ከቀረበው ጥያቄ አንፃር ሲታይ ባንኮች ያቀረቡት የብድር መጠን አነስተኛ የሚባል ነው፡፡ የባንኮችን 2008 በጀት ዓመት የብድር መጠን የሚያመለክተው መረጃ፣ በሚቀርበው፣ የብድር ጥያቄ ልክ ብድር ለመስጠት ካልቻሉባቸው ምክንያቶች አንዱ የባንኮች አቅም ውስን ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ የሚሰጡት ብድርም ንብረት ማስያዝ ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ በእጃቸው ያለውን ገንዘብ እንኳ እንደ ልብ ያለማበደር ችግር ይታይባቸዋል፡፡ የብድር አሰጣጣቸው ፈጣን ትርፍ በሚያስገኙ ዘርፎች ላይ ያተኮረ መሆኑም ከብድር አሰጣጥ ጋር የሚታይ ችግር ሆኖ ለረዥም ጊዜ ቆይቷል፡፡

  እንደ ብድር አቅርቦቱ ዕድገት ሁሉ የባንኮች የተቀማጭ ገንዘብም በ2008 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ከ147 ቢሊዮን ብር በላይ ሊያስመዘግብ ችሏል፡፡ የደንበኞቻቸውን የብድር ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ መመለስ ያስቻለ ግን አልነበረም፡፡

  የግል ባንኮች ለደንበኞቻቸው ከሚሰጡት ከእያንዳንዱ ብድር 27 በመቶ ለቦንድ ግዥ እንዲያውሉ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያም፣ ለገበያው ማቅረብ የነበረባቸውን ያህል ብድር እንዳይሰጡ ተፅዕኖ ማድረጉን የሚጠቅሱ አሉ፡፡

  ምንም እንኳ ባንኮች ከአምስት ዓመታት በፊት ለቦንድ ግዥ ያዋሉት ገንዘብ ጊዜው ደርሶ ተመላሽ መደረግ ቢጀምርም፣ ለዓመታት የተከማቸውና ለቦንድ ግዥ ያዋሉት ገንዘብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ የማበደር አቅማቸው ላይ ጫና ሲያሳድር ቆይቷል፡፡ በ2008 ዓ.ም. መጨረሻ የግል ባንኮች ለቦንድ ግዥዎች ያዋሉት ገንዘብ መጠን ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ለዚህ ማሳያ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

  የአገሪቱ የግል ባንኮች በሚፈለገው ደረጃ ብድር እየሰጡ ባይሆኑም፣ ራሳቸውን በማደራጀቱ ረገድ የተሻለ ውጤት እያሳዩ መምጣታቸው ይነገራል፡፡ እንደምሳሌ የሚቀርበውም የ16ቱ ባንኮች ሀብት ከ192 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ነው፡፡ ይኸውም የባንኮች አቅም እየጠነከረ መምጣቱን ቢያሳይም፣ የካፒታላቸው መጠን ግን አሁንም ያን ያህል ዕድገት ያልታየበት ነው ተብሏል፡፡ 16ቱም የግል ባንኮች ያስመዘገቡት አጠቃላይ ካፒታል መጠን 25.7 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታላቸው ግን 15.8 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡

  35 ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞችን የሚያስተዳድሩት የአገሪቱ የግል ባንኮች፣ የቅርንጫፍ ቁጥራቸውን ብዛትም 2,000 ያደረሱ ሲሆን፣ የ2008 በጀት ዓመት ትርፋቸውም ከ6.3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

   

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች