Wednesday, August 10, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበአዲስ አበባ የአተት በሽታ ሥርጭት መጨመሩ ተገለጸ

  በአዲስ አበባ የአተት በሽታ ሥርጭት መጨመሩ ተገለጸ

  ቀን:

  በአዲስ አበባ ከወር በፊት የተከሰተው አተት (አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት) ከመቀነስ ይልቅ መጨመሩን፣ ለዚህም ምክንያቱ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች የተበከለ የወንዝ ውኃን በመጠቀማቸው እንደሆነ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

  የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመድ ኢማኖ ይህን የገለጹት፣ ሰሞኑን ለመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች በአተት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ሲደረግ ነው፡፡

  የወንዝ ውኃ ለሕገወጥ ዕርድ፣ ለዕቃ ማጠቢያና አትክልት ለማጠጣት ጥቅም ላይ መዋሉ ችግሩን ካባባሱት ይጠቀሳል፡፡ ነዋሪው በሽታውን የመከላከያ ዘዴዎቹን ሙሉ ለሙሉ ተግባር ላይ አለማዋሉም ለበሽታው መስፋፋት ምክንያት ሆኗል፡፡

  አተት በታዳጊ አገሮች፣ የጎርፍ፣ የድርቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የጦርነትና የመሳሰሉ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰቱና ከተከሰቱ በኋላ ሊከሰት የሚችል በሽታ ሲሆን፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሊከሰትም ይችላል፡፡

  በድህነትና በተለያዩ ምክንያቶች በአንድ አካባቢ ተፋፍገው ወይም ተጨናንቀው በሚኖሩ ሰዎች ላይ በቀላሉ ሊከሰት የሚችል በሽታ ሲሆን፣ በተበከለ ውኃ ምግብ ወይም በበሽታው በተያዙ ሰዎች አማካይነት ከቦታ ቦታ ሊዛመት ይችላል፡፡

  በሽታው በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽን በተቅማጥና ትውከት መልክ በመጨረስ አቅምን የሚያዳክምና ሰውነትን የሚያዝል ሲሆን፣ አፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገ በጥቂት ሰዓት ውስጥ ለሞት ይዳርጋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹ምዕራባውያን አፍሪካውያንን ለማዘዝ የሚያሳዩት ፍላጎት ተቀባይነት የለውም››

  የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንደር የአሜሪካ የውጭ...

  ዕውቅና ቤት ለቤት ልብስ ለሚያጥቡ ሴቶች

  ሴቶች በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን፣ መላው...

  በኮሎምቢያ ካሊ በወጣት አትሌቶች በሜዳሊያ የተንበሸበሸው ብሔራዊ ቡድን ዓርብ አቀባበል ይደረግለታል

  በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የዓለም ወጣቶች...

  የፌዴሬሽኑ ቀጣይ ምርጫና የሊጉ አክሲዮን ማኅበር መግለጫ

  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ...