Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  ‹‹አማረች አዲስ አማረች››

  ትኩስ ፅሁፎች

  ስለአዲስ አበባ ሲነሳ ከመልካም ገጽታዎቿ ባልተናነሰ የንፅህና ጉድለቷም ይነሳል፡፡ ብዙ አካባቢዎች የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ መዋያ ማደሪያ ሆነዋል፡፡ የችግሩ ሥር መስደድ ያሳሰባቸው ነዋሪዎችም ‹‹የአፍሪካ መዲና የሆነች ከተማ እንዴት ከቆሻሻ መፅዳት ተሳናት?›› የሚል ጥያቄ ሲሰነዝሩ ይስተዋላል፡፡ ሐምሌ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ከደጐል አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ እስከ አመሻሽ ድረስ ቆሻሻ አልተነሳም ነበር፡፡ ወደ አራት የሚደርሱ የቆሻሻ ክምሮች በመተላለፊያ መንገድና በሱቅ ፊት ለፊት እንደተቆለሉ አምሽተዋል፡፡ (ፎቶ በምሕረተሥላሴ መኰንን) * * * ነገ አመድ ትቢያ ለመሰለው በአልጋ ለዋለው ታሞ በሐዘን ልቡ ለተሰበረ የኑሮን ዳገት ሲቧጥጥ ከርሞ ተስፋው አንቺ ነሽ ነገ ለሚያስብሽ ዛሬ ላይ ቆሞ፡፡ ታዬ አስፋው፣ ሐጢሾ (2008) * * * ከአምስት ዓመት አገልግሎት በኋላ እድገት ያገኘችው ድመት እንግሊዝ ውስጥ የሀደርስፊልድ ባቡር ጣቢያ ላለፉት አምስት ዓመታት ያለመታከት አይጥ አድኖ በመያዝ ሥራ ያገለገለችውን ፍሌክስ የተባለች ድመት እድገት ሰጥቷታል፡፡ የጣቢያው ኃላፊዎች ለዘ ኢንዲፔንደንት፣ ድመቷ ቀን ከሌሊት ያለመታከት ለጣቢያው ላበረከተችው አስተዋጽኦ እድገት ይገባታል ብለዋል፡፡ ፍሌክስ የጣቢያው የእንስሳት ቁጥጥር ኃላፊ ተብላ የተሾመች ሲሆን፣ ጃኬትና ስሟን ከኃላፊነቷ ጋር የያዘ ባጅ ተበርክቶላታል፡፡ ድመቷ ጣቢያውን የተቀላቀለችው የዘጠኝ ወር ሙጭሊት ሆና ሳለ ነበር፡፡ አሁን በባቡር ጣቢያው ሠራተኞችና በአካባቢውም ተወዳጅነት አትርፋለች፡፡ የምታደርገው እንቅስቃሴ በአጠቃላይ የሚገለጽበት የፌስቡክ ገጿ ከ17,000 በላይ ወዳጆች አሉት፡፡ * * * የታይዋኑ የንግሥት ራስ ቅርጽ የንግሥት ራስ ቅርጽ ያለውን የታይዋን ተፈጥሯዊ አለት በዓመት ከ3 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች ይጐበኙታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን አለቱ በተለያዩ ተፈጥሯዊ አደጋዎች ሳቢያ እየተሸራረፈ በመሆኑ የአገሪቱ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ለቻይና ዴይሊ አሳውቋል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከአለቱ አንገት 12 ሴንቲ ሜትር ያህል ተሸርፏል፡፡ የባህር ውኃ፣ ንፋስና የመሬት መንቀጥቀጥ የቱሪስት መስህባቸውን እንዳያሳጣቸው የሰጉት ቅርስ ጠባቂዎች፣ አለቱን በመስታወት ለመሸፈን ቢያስቡም፣ መስታወቱ ቢሰበር የሚያደርሰውን ጉዳት በመፍራት ትተውታል፡፡ ቅርሱ የሚጠበቅበት ሐሳብ ለሚያመነጭ ድርጅት ኃላፊነት ለመስጠት ጨረታ ማውጣታቸውም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ * * * ቤት የተሳሳተው ታዳጊ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱን አጣ በስካር መንፈስ አልያም በሌላ ቤት ተሳስቶ የሌላ ሰው መኖሪያ ቤት ማንኳኳት የብዙዎች የተለመደ ገጠመኝ ነው፡፡ አጋጣሚውም በይቅርታ የሚታለፍ ነው፡፡ ሰሞኑን ከወደ አሜሪካ አካባቢ የተሰማው ግን ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ የ15 ዓመቱ ታዳጊ ከአንድ ጓደኛው ጋር መጠጥ ሲጠጡ ቆይተው ሞቅታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ሌላ አንድ ጓደኛቸው ይቀላቀላቸው ዘንድም በስካር መንፈስ ወደ ጓደኛቸው መኖሪያ ቤት ገሰገሱ፡፡ መኖሪያ ቤቱ ደርሰውም በሩን ማንኳኳት ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ተሳስተው ኖሮ ያንኳኩት የሌላ ሰው ቤት ነበር፡፡ የቤቱ ባለቤት የ42 ዓመቱ ጄፍሪ ሌቭል ነገሩን እንደ ቀላል አላለፈውም፡፡ በሩን ሲያንኳኳ ወደነበረው ደይሌን ፍራንሲስኮ ላይ ተኮሰበት፡፡ ታዳጊውም ሕይወቱ አለፈ፡፡ ተጠርጣሪው ጄፍሪም በግድያ ወንጀል ክስ ተመሥርቶበት በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የቺኮፒ ፖሊስ ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡ – ዋሺንግተን ፖስት * * * ባህር ውስጥ ጠልቆ የጠፋው ካሜራ ተገኘ በአትላንቲክ ኦሸን አካባቢ በሚገኘው ሰሜን ባህር ውስጥ ከሦስት ዓመታት በፊት ጠልቆ የጠፋው ፉጂ የፎቶ ካሜራ ለባለቤቷ ተመለሰላት፡፡ ካሜራው ለባለቤቲቱ የተመለሰው፣ ውኃ ወደ ውስጥ እንዳይገባ በሚከላከል ፕላስቲክ በመታሸጉና በውስጡ ያሉት ፎቶዎች ባለመበላሸታቸው፣ የማን መሆኑን በቀላሉ ለመለየት በመቻሉ ነው፡፡ የካሜራው ባለቤት ጠላቂዋ አዴል ዲቮንሽር ካሜራው የጠፋባት ከሦስት ዓመት በፊት በሰሜን ባህር ውስጥ በምትጠልቅበት ወቅት መሆኑን፣ በውስጡም በርካታ ፎቶ ግራፎች መኖሩን ተናግራለች፡፡ ይህ ካሜራ የተገኘው ከጠፋበት ቦታ 854.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጉልሆልምን በተባለች ደሴት ላይ ነበር፡፡ ካሜራውን ያገኘው ላርስ ሞስበርግ የተባለው የደሴቷ ነዋሪ ሲሆን ካሜራ ማግኘቱንና በካሜራው ውስጥ ያሉትን ፎቶግራፎች በፌስቡክ ገጹ ላይ በመለጠፍ የካሜራውን ባለቤት ማወቅ መቻሉን ገልጿል፡፡ – ሚረር

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች