Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የደቡብ ቡና አቅራቢዎች የባንክ ዕዳ ወደ መንግሥት ባንክ እንዲዛወር ዕድል ተሰጠ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ቡና አቅራቢዎች ብቻ በሐዋሳ ከተማ ከ2,400 በላይ ቤቶችን ለብድር አስይዘዋል

  በደቡብ ክልል ለሚገኙ ቡና አቅራቢዎች ያጋጠማቸውን ኪሳራ ተከትሎ በተለያዩ የግል ባንኮች ያሉዋቸው ብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ከተላለፈው ውሳኔ ጎን ለጎን በግል ባንኮች ያለባቸው ዕዳ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዛወር የሚያስችል ዕድል እንደተሰጣቸው ተገለጸ፡፡

  የደቡብ ክልል የቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች ዘርፍ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት ለቡና አቅራቢዎች የባንክ ዕዳ መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ከወሰነው ውሳኔ ሌላ በግል ባንኮች ያለውን ዕዳቸውን ወደ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዛወር ይችላሉ፡፡

  ተደጋጋሚ የብድር መክፈያ ማራዘሚያ ጊዜ የተሰጣቸው እነዚህ ቡና አቅራቢዎች፣ ብድሩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዛወር የሚችሉት በፍላጎት ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ይህንን የመንግሥት ውሳኔ የሚገልጽ ደብዳቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች እንደተሠራጨም አቶ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡

  በቅርቡ በሁለት ተከታታይ ሰርኩላሮች እነዚህ በደቡብ ክልል የሚገኙ ቡና አቅራቢዎቹ ለባንክ ብድር ማስያዣነት ያዋሉት ንብረት ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሸጥ፣ የብድር መክፈያ ጊዜያቸው እንዲራዘምና ተጨማሪ ብድር እንዲያኙ ዕድል እንዲሰጣቸው ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

  ከዚህ ሌላ መንግሥት ቡና አቅራቢዎቹን ለመደገፍ ካስተላለፈው ሰርኩላር ጎን ለጎን ብድራቸው ወደ መንግሥት ባንክ እንዲዛወር የተፈለገው ማኅበሩ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

  አቶ ዘሪሁን እንደገለጹት፣ የማኅበሩ ፍላጎት በግል ባንኮች ያለው ዕዳ ሙሉ ለሙሉ ወደ ንግድ ባንክ እንዲዛወር ቢሆንም መንግሥት ግን የዕዳ ዝውውሩ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ይሁን በሚል በመወሰኑ በዚሁ መሠረት ተስተናግዷል፡፡ ይገደብ እንጂ ፍላጎታችን ሁሉም ብድር ወደ መንግሥት ይዛወር የሚል ነበር፤›› ብለዋል፡፡

  ማኅበሩ ይህንን ሐሳብ ያቀረበው መንግሥታዊው ባንክ ብድሩን ለማስታመም የተሻለ ጊዜ ይሰጣል ከሚልና የወለድ ምጣኔውም ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ ከአቶ ዘሪሁን ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

  የዕዳ ዝውውሩ ወደ መንግሥት ባንክ የሚዛወረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግል ባንኮች ያለውን ዕዳ ከፍሎ ሲያዛውረው ነው፡፡ እነዚህ የደቡብ ቡና አቅራቢዎች ከተለያዩ ባንኮች የተበደሩት ብድር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን፣ ብድሩ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣ ነው፡፡ ከባንክ ለወሰዱት ብድርም በሐዋሳ ከተማ ብቻ ከ2,400 በላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች አስይዘዋል፡፡ መንግሥት ይህን ውሳኔ የሰጠው የሚፈጠረውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመታደግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

  አቶ ዘሪሁን እንደገለጹት፣ መንግሥት የብድር ማራዘሚያና ንብረቶቹም እንዳይሸጡ ማድረጉ ቡና አቅራቢውን ብቻ ሳይሆን ቡና አቅራቢዎች ብድር እንዲያገኙ ቤቶቻቸውን ለባንክ ብድር ማስያዣ ያዋሉ ዜጎችን የታደገ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ትልቅ ቀውስ እንደሚፈጠር ገልጸው፣ ‹‹የመንግሥትን ውሳኔ ያልታሰበና ሕዝባዊነቱን ያሳየበት ነው፤›› ብለዋል፡፡

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች