Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበሕወሓት ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ ተገለጸ

  በሕወሓት ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ ተገለጸ

  ቀን:

  ከጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የከፍተኛ አመራሮች ኮንፈረንስ፣ በማዕከላዊ ኮሚቴው ግምገማ ወቅት እንደተደረገው ሁሉ እስከ ታችኛው ድረስ ባሉ የድርጅቱ መዋቅሮች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገለጹ።

  አቶ ጌታቸው ይህን የገለጹት ማክሰኞ ጥር 8 ቀን 2010 ዓ.ም. መቀሌ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ አዳራሽ አጠቃላይ የኮንፈረንሱን ሒደት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው።

  በዚህም መሠረት እስካሁን በቀረቡ ሪፖርቶችና ውይይቶች ላይ በመመሥረት በሚገኙ ውጤቶች መነሻነት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አሁን ያለው ካቢኔም ሆነ በየደረጃው ያለው አመራር የጥፋቱ አካል ስለሆነ የመፍትሔውም አካል መሆን አለበት። ነገር ግን በዚህ ውይይት ላይ ተመሥርቶ የጥፋቱ አካል ሆኖ፣ ነገር ግን የመፍትሔ አካል መሆን እንደማይችል የተረጋገጠበት ሰው ካለ ይዘን የምናዘግምበት ምክንያት አይኖርም። በተጨማሪም ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ሆኖ መፍትሔ ከመስጠት አንፃር እንቅፋት ሊሆን የሚችል አሠራርና አደረጃጀት ካለ እርሱም ይፈተሻል፤›› ብለዋል።

  ‹‹ኮንፈረንሶች የንግግር ሱስ የምንወጣበት መድረክ አይደሉም፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ በዚህም መሠረት በመካሄድ ላይ ያለው ኮንፈረንስ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ነው በማለት አስረድተዋል።

  በመካሄድ ላይ ያለው ኮንፈረንስ እስካሁን ከተደረጉ ኮንፈረንሶች በተለየ አዲስ የሚያደርገው አገሪቱንና ክልሉ ያሉበት ሁኔታ እንደሆነ ገልጸው፣ ‹‹የኮንፈረንሱ መነሻ አመራሩ በፈጠረው ችግር ምክንያት አገር ትልቅ የአደጋ አፋፍ ላይ መሆኗ፣ እንዲሁም የሕዝባችን የኑሮ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ የሆነ ደረጃ አድርሰናል የሚል መነሻን መሠረት ያደረገ ነው፤›› ሲሉ ገልጸዋል።

  ‹‹ይህንን ሁኔታ በተለመደው የለብለብ ግምገማ ልንፈታው አንችልም፡፡ መጨረሻ ላይ አገርንም ሕዝብንም ወደማይሆን ገደል ልንከት እንችላለን ከሚል ቁርጠኛ ግምገማ ላይ ተመሥርተን የምናካሂደው ከመሆኑም በላይ፣ አማራጭ የለንም ብለን የገባንበት ነው፤›› በማለት አስረድተዋል።

  በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በአሥር ቡድኖች ተከፋፍለው ውይይት እያካሄዱ ሲሆን፣ ከሰኞ ጥር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ቡድኖቹ በውይይታቸው ላይ ተመሥርተው የሚደርሱባቸውን ግኝቶች ለአጠቃላይ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች እያቀረቡና እየተወያዩ ነው ተብሏል።

  በውይይቱ ላይ በርካታ ጉዳዮች እየተነሱ ሲሆን፣ በተለይ ከመልካም አስተዳደርና ከልማት ሥራዎች ጋር በተያያዘ ብዙ ርቀት አለመጓዝ ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚገባውን የኃላፊነት ልክ ማስቀመጥ፣ እንዲሁም ከሙስናናብልሹ አሠራር አንፃር የሚነሱ ጥያቄዎችን ዕልባት ለመስጠት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ የግድ መሆኑ ከተነሱት ጉዳዮች መካከል የሚጠቀሱት ናቸው።

  ውይይቱ ዓርብ ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከመጠናቀቁ በፊት በማዕከላዊ ኮሚቴ ላይ በዝርዝር የሚቀርቡሶችና ግለ ሒስች ላይ ተመሥርቶ፣ አስፈላጊ የእርምት ዕርምጃዎች እንደ ሁኔታው የሚወሰድበትድል እንደሚፈጠር አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል። በየደረጃው ባሉ መዋቅሮችም አመራርና አሠራር ላይ ለውጥ እንደሚኖር አክለዋል፡፡

  በአሁኑ ኮንፈረንስ በትግራይ ክልልና በአገሪቱ ያጋጠሙ ችግሮችን ከአባል ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመፍታት ግምገማ መካሄዱን፣ በችግሮቹ መንስዔዎች ላይም ዕርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

  የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው 35 ቀናት ግምገማ፣ ሒስና ግለ ሒስ ከተደረገ በኋላ ዘጠኝ አባላት ያሉት የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄዱ ይታወሳል።

  የትግራይ ክልል ምክር ቤት በቅርቡ ባደረገው ስበሰባ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን (/) ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ የሚታወስ ሲሆን፣ እሳቸው የፕሬዚዳንቱን ሥራ በሙሉ ኃላፊነት እንዲያከናውኑ መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ዓባይ ወልዱ ደግሞ ከፕሬዚዳንትነታቸው በምክር ቤቱ ተሰናብተዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...