Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኢትዮጵያና የሶማሊያ ሠራዊት የአልሸባብን ጥቃት መመከታቸው ተገለጸ

  የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሠራዊት የአልሸባብን ጥቃት መመከታቸው ተገለጸ

  ቀን:

  የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና የሶማሊያ ሠራዊት ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ንጋት ላይ የማጥቃት ሙከራ ያደረገባቸውን የአልሸባብ 245 ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ አልሸባብ በበኩሉ 60 ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን በጥቃቱ እንደገደለ እየገለጸ ይገኛል፡፡

  የኢትዮጵያ መከላከያና የሶማሊያ ሠራዊት በወሰዱት የመከላከልና ፀረ ማጥቃት ዕርምጃ አምስት ከፍተኛ የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ 245 ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን ያመለከተው የመከላከያ ሠራዊት መግለጫ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎችም መማረካቸውን ይገልጻል፡፡

  አልሸባብ በሶማሊያ ሃልገን ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረገው የማጥቃት ሙከራ ለደጋፊዎቹ ቡድኑ በሕይወት እንዳለ መልዕክት ለማስተላለፍና የደጋፊዎቹን ሞራል ለማነሳሳት እንደሆነ የገለጹት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በጥቃቱ የሞቱትንም ሆነ የተጎዱትን ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በትዊተር አካውንታቸው ‹‹የአልሸባብ አባላት የማይነካውን ሠራዊት በመተናኮላቸው መቼም የማይረሱ ትምህርት አግኝተዋል፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

  የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ የአልሸባብ የጥቃት ሙከራ እንደሚያወግዙ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትን ጨምሮ በሶማሊያ ያለውና ከስድስት አገሮች የተዋቀረው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) 22,000 ወታደሮች አሉት፡፡ ዶ/ር ዙማ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ወታደሮች ጥቃቱን ለማክሸፍ የነበራቸውን ፈጣን ምላሽና ጀግንነት አድንቀዋል፡፡ ሊቀመንበሯ አፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ዘላቂ ልማት እስኪረጋገጥ ድረስ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር መሥራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

  የአልሸባብ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ቃል አቀባይ አብዲ አሲስ አቡ ሙሳብ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ግን በጥቃቱ የተገደሉት የአልሸባብ አባላት 16 ብቻ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያውያን ወታደራዊ መሠረት ላይ ከአራት አቅጣጫ የተፈጸመው ጥቃት ብዙ ጉዳት እንዳስከተለም አክለዋል፡፡

  የአሚሶም ቃል አቀባይ ሉተናንት ኮሎኔል ጆይ ኪቤት አልሸባብ ገደልኩ ያለውን 60 ወታደሮች ‹‹ውሸት›› ያሉ ሲሆን፣ በአሚሶም ላይ የደረሰውን ጥቃት የጉዳት መጠን እንደ አቶ ጌታቸው ሁሉ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

  አልሸባብ እ.ኤ.አ. በ2006 በኢትዮጵያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ከወደመው የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት የተገነጠለ ቡድን ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የሽብር ቡድን ከሆነው አልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ቡድኑ በተለያዩ ጊዜያት በአሚሶም ላይ ጥቃት የሚሰነዝር ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ላይ ግን ይህን ሲያደርግ የመጀመርያው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...