Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናእነ አቶ በቀለ ገርባ በፍርድ ቤት መኖራቸውን በድምፅ አላረጋገጡም  ተብለው ችሎት የመድፈር...

  እነ አቶ በቀለ ገርባ በፍርድ ቤት መኖራቸውን በድምፅ አላረጋገጡም  ተብለው ችሎት የመድፈር ቅጣት ተጣለባቸው

  ቀን:

  በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸውን ወይም ጥፋተኛ ሳይሆኑ በነፃ መሰናበታቸውን ለመንገር በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ለፍርድ ተቀጥረው የነበሩት እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ የስድስት ወራት እስር ቅጣት ተጣለባቸው፡፡

  ተከሳሾቹ የእስር ቅጣቱ የተጣለባቸው በችሎት መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ፍርድ ቤቱ በስም ሲጠራቸው ምላሽ ባለመስጠታቸው፣ ‹‹ፍርድ ቤት የመድፈር ወንጀል ፈጽመዋል›› በማለት ነው፡፡

  በአቶ አያና ጉርሜሳ የክስ መዝገብ ውስጥ ከተካተቱት 22 ተከሳሾች መካከል አቶ አያና ጉርሜሳ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲ ቡላና አቶ በቀለ ገርባ ለፍርድ መቀጠራቸውን በማስታወስ ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ስማቸውን ቢጠራም ምንም ዓይነት ምላሽ መስጠት አልፈለጉም፡፡

  ፍርድ ቤቱ ‹‹የማትነሱና ማንነታችሁን የማታረጋግጡ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ዕርምጃ ይወስዳል፤›› ሲል፣ ጠበቆቻቸው መኖራቸውን በድምፅ እንዲያረጋግጡ ተከሳሾቹን በመጠጋት መለመን ጀመሩ፡፡ ተከሳሾቹ በአቋማቸው በመፅናታቸው ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ መናገር እንደማይፈልጉ ገለጹ፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹አለመናገር መብታቸው ነው፡፡ ግን መምጣታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀጠሮ ስላላቸው ነው፡፡ ይኼ ፍርድ ቤቱን አለማክበርና የፍርድ ቤቱን ሥራ ማደናቀፍ ነው፤›› ብሏል፡፡

  ጠበቆች በመሀል ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ምላሽ ችሎቱ ፊት ለፊት እያያቸው ስለሆነ ፍርዱን እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ደግሞ በሰጠው ምላሽ ችሎቱ የፍትሐ ብሔር ሳይሆን የወንጀል ችሎት መሆኑን ገልጾ ሕግ እንደማይፈቅድ አስረድቷል፡፡ በዚህ መሀል ፍርድ ቤቱ እንደገና ስማቸውን ሲጠራ ተከሳሾች ያለ ድምፅ እጃቸውን ያወጡ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ግን መኖራቸው የሚረጋገጠው በድምፅ መኖራቸውን ሲያረጋግጡ መሆኑን አስታውቋል፡፡

  የተከሳሾቹ ጠበቆች የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርኛት ሕግ ቁጥር 127 በመጥቀስ ተከሳሾች ምላሽ አለመስጠት መብታቸው እንደሆነና እነሱን ወክለው ጠበቆች መናገር የሚችሉ መሆኑን ቢናገሩም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾቹ ሰኞ ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው ፍርድ ለመስጠት ቢሆንም፣ ተከሳሾቹ በችሎት ተገኝተው ስለመቅረባቸው ለማረጋገጥ ስማቸው ሲጠራ ምላሽ ባለመስጠታቸውና ለ30 ደቂቃዎች ያህል የፍርድ ቤቱን ሥራ በማወካቸው፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 449 (1ለ) ሥር የተደነገገውን ተላልፈዋል በማለት ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

  ቀደም ብሎ በነበረ ችሎት ችሎት በመድፈር ወንጀል በስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም፣ ሊማሩበት አለመቻላቸውን በመጠቆም በድጋሚ በስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

  በመዝገቡ ላይ ፍርድ ለመስጠትም ለየካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

  ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ የአገሪቱ...

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...