Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልአዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ

  አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ

  ቀን:

  ‹‹ትስስር›› እና ‹‹ዋሳ›› በዘጠነኛው አዲስ ኢንተርናሽናል የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለእይታ ከሚበቁ ፊልሞች መካከል ሁለቱ ናቸው፡፡ ‹‹ትስስር›› ትኩረቱን ያደረገው ባህልን ማንፀባረቅ ላይ ሲሆን፣ ‹‹ዋሳ›› ስለተፈጥሮ ሀብት ያትታል፡፡ ዘጋቢ ፊልሞቹ በሰኔው ፌስቲቫል እንዲቀርቡ የተመረጡ የኢትዮጵያ ፊልሞች ናቸው፡፡

  ፌስቲቫሉ ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከአውሮፓ የተውጣጡ ከ60 በላይ ዘጋቢ ፊልሞችንም ያስተናግዳል፡፡ ከበርካታ አገሮች የተመረጡ የፊልም ባለሙያዎች ፌስቲቫሉን እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡ በፌስቲቫሉ ከሚቀርቡ ዓለም አቀፍ ፊልሞች በልዩ ልዩ ውድድሮች ዕጩ ሆነው የቀረቡት ‹‹ሲቲዝን ፎር››፣ ‹‹ኮንሰርኒንግ ቫዮለንስ››፣ ‹‹ኤቫፓሬቲንግ ቦርደርስ›› እና ‹‹ኤሌፋንትስ ድሪም›› ይጠቀሳሉ፡፡

  በፌስቲቫሉ ስለሚታዩት ፊልሞች እንዲሁም በፊልም ሥራ ዙሪያ ውይይት እንዲያደርጉ የእንግሊዝ፣ የጓቲማላ፣ የህንድ፣ የካሜሩን፣ የእስራኤልና የፈረንሳይ የፊልም ባለሙያዎች ተጋብዘዋል፡፡ ወጣትና አንጋፋ ኢትዮጵያውያን ፊልም ሠሪዎችም የውይይቱ ተካፋይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

  ከፌስቲቫሉ አስተባባሪዎች አንዷ የምሥራች አጥናፉ ለሪፖርተር እንደገለጸችው፣ ዘጋቢ ፊልሞቹ ከታዩ በኋላ የፊልሙ አዘጋጆችና ፕሮዲውሰሮች ከታዳሚው ጥያቄ ይቀበላሉ፡፡ ስለ ፊልሙ አሠራር ቴክኒክና ጭብጥ ውይይት ይደረጋል፡፡ ፊልሞቹ በየተሠሩበት አገር ያለውን ማኅበራዊ ሁኔታ የሚያሳዩ በመሆናቸው ለልምድ ልውውጥ አመቺ እንደሆነ ገልጻለች፡፡

  በዋነኛነት ዘጋቢ ፊልሞችን የሚያስተናግደው አዲስ ኢንተርናሽናል የፊልም ፊስቲቫል ላይ የሚቀርቡ ፊልሞች ከሚዳስሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአካባቢ ጥበቃ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የሥነ ጾታ ጉዳይና ሌሎችም ማኅበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

  የፌስቲቫሉ መክፈቻ ሰኔ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ይሆናል፡፡ እስከ ሰኔ 9 ድረስ በሐገር ፍቅር ቴአትር፣ በብሪትሽ ካውንስልና አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ ፊልሞች ይታያሉ፡፡

  በኢኒሽየቲቭ አፍሪካ የሚሰናዳውና በ2002 ዓ.ም. የተጀመረው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት አገር ውስጥና ውጪ የተሠሩ አያሌ ዘጋቢ ፊልሞችን አስተናግዷል፡፡ በርካታ ፊልም ሠሪዎችን ከተለያዩ አገሮች በመጋበዝና የውይይት መድረክ በመፍጠርም ይታወቃል፡፡ በፌስቲቫሉ ተሳታፊ አገሮች የሚገኙበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያንጸባርቁ ፊልሞችን ለበርካታ ታዳሚዎች በማሳየትም ፌስቲቫሉ ይጠቀሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...