Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየቴዲ ምትኩ ሳክስፎን ለጨረታ ቀረበ

  የቴዲ ምትኩ ሳክስፎን ለጨረታ ቀረበ

  ቀን:

  የዝነኛው ሙዚቀኛ ቴዎድሮስ ምትኩ (ቴዲ) ሳክስፎን በአሜሪካ ኢቤይ ላይ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ ታህሣሥ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ቴዲ ሙዚቃ ይጫወትበት የነበረው አልቶ ሳክስፎን ለጨረታ የቀረበው በባለቤቱ ሲሆን፣ በጥሩ ይዞታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ታዲያስ ሜጋዚን የሳክስፎኑን አሻሻጭ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሳክስፎኑ በጥንቃቄ ስለተያዘ በጥሩ ሁኔታ ነው ለገበያ የቀረበው፡፡

  ዘገባው አክሎ እንደገለጸው ሳክስፎኑ የፀዳ ሲሆን፣ ለሽያጭ በሚያመች መልኩም ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ለዓመታት አገልገሎት መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ የተለያዩ የሙዚቃ ዘዬዎችን ለመጫወት የሚያስችል ሲሆን፣ አርኤንድቢና ጃዝን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ጨረታውን በዋነኛነት የምትመራው ባለቤቱ መዓዛ በዙ መሆኗ ታውቋል፡፡

  ሙዚቀኛው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ባንድ ‹‹ሶል ኢኮስ›› አባል ነበር፡፡ በ1960ዎቹና 70ዎቹ በኢትዮጵያ ታዋቂ ለነበሩ ባንዶች ምሥረታም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በበርካታ ሙዚቃ አፍቃሪዎች የተደነቀ የመሣሪያ አጨዋወት ዘዬ ነበረው፡፡

  ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር በነበረበት ወቅት ጥላሁን ገሠሠና የኢትዮ ጃዝ አባቱ ሙላቱ አስታጥቄን ከመሰሉ ዝነኛ ሙዚቀኞች ጋር በጥምረት ሠርቷል፡፡ አይቤክስ ባንድ ውስጥ ሳክስፎን ይጫወት በነበረበት ወቅት የሠራው የመሐሙድ አህመድ ተወዳጅ ዘፈን ‹‹ኧረ መላ መላ›› ይታወሳል፡፡

  ታዋቂው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ ወንድም የነበረው ሙዚቀኛው፣ ከ1975 ዓ.ም. ጀምሮ አሜሪካ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡

  የቴዎድሮስ ሳክስፎን ድምፅ ከሚሰማባቸው ሙዚቃዎች የወንድሙ ተሾመ ሥራዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ሙዚቃን የጀመረውም በኮከበ ጽባህ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ከወንድሙና ሌሎች ሙዚቀኞች ጋር ነበር፡፡

  በ1987 ዓ.ም. የታተመውና በመሣሪያ የተቀነባበረው ‹‹የቴዲ ስሜት›› አልበም ላይ የተካተተው ‹‹አማሌሌ›› በብዙዎች ተወዳጅነት አትርፎለታል፡፡ መስከረም ሲጠባ፣ የፍቅር ከተማ፣ ትዝታ፣ እንደው ዘራፌማ፣ የሕይወቴ ሕይወት ሌሎች ታዋቂ ሥራዎቹ ናቸው፡፡

  Previous article‹‹ዙቤይዳ››
  Next articleምን የት?
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...