Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትየቀድሞው የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ጃክ ሮክ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጎበኙ

  የቀድሞው የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ጃክ ሮክ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጎበኙ

  ቀን:

  –  በጋምቤላ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በስፖርት እንዲሳተፉ ዕርዳታ እንደሚደረግላቸው ተገለጸ

  የቀድሞ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ፕሬዚዳንትና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ልዩ መልዕክተኛ ጃክ ሮክ ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጎበኙ፡፡ ጃክ ሮክ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ወጣት ስደተኞች እንደየዝንባሌዎቻቸው በስፖርት እንዲሳተፉ ዕድል እንደሚመቻችላቸው ቃል መግባታቸውም ታውቋል፡፡

  የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ስምንተኛው የአይኦሲ ፕሬዚዳንት የነበሩትና ተቋሙን ለተከታታይ አሥራ ሁለት ዓመታት የመሩት ጃክ ሮክ    የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውን አደረጃጀት፣ የአሠራር ሥርዓትና ተቋሙ እስካሁን በሥራ እንቅስቃሴው ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት ያደረገውን አስተዋጽኦ፣ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያና መሰል ጉዳዮች ላይ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ኃላፊውም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የጀመረውን ተቋማዊ አደረጃጀት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

  የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የነበረውን ጊዜ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ጋምቤላ ተጉዞ በክልሉ የሚገኙትን የደቡብ ሱዳን ወጣት ስደተኞችን ጎብኝቷል፡፡ ስደተኞቹ በስፖርት ራሳቸውን እንዲያዳብሩ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የቀድሞ የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ቃል መግባታቸውም ተሰምቷል፡፡

  ጃክ ሮክ በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወጣት ስደተኞች ልዩ መልዕክተኛ በመሆን እያገለገሉ ይገኛል፡፡ በመሆኑም መልዕክተኛው በማንኛውም ሁኔታ ስፖርት ለሰው ልጆች ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዳለው፣ በተለይም ስደተኞች በሚጠለሉባቸው ጣቢያዎች ለሚገኙ ወጣቶች እንደየዝንባሌያቸው የተለያዩ ውድድሮችን እንዲያከናውኑ እርስ በርሳቸው እንዲግባቡና እንዲተባበሩም ለማድረግ የጎላ ድርሻ እንዳለው ጭምር መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

  በተጨማሪም ስደተኞች ተጠለው በሚገኙባቸው ቦታዎችና ጣቢያዎች የሚገኙ ወጣቶች፣ ስፖርት እንዲያዘወትሩ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማሟላት ጠንክረው በመሥራት ሕልምና ምኞታቸውን እንዲያሳኩ ምኞታቸው እንደሆነም የቀድሞው ፕሬዚዳንት መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡

  ከ285,000 በላይ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ይነገራል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች የተለያዩ ውድድሮችን በማድረግ ወጣቶቹ በትምህርት ውጤታማ ጊዜን እንዲያሳልፉና በአካባቢው ከሚገኙ ማኅበረሰብ ጋር አብረው ለማዋሀድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

  የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃክ ሮክ በጉብኝታቸው የስደተኞች ቤተሰቦች፣  ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊዎች ጋር በመሆን በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በእጅ ኳስና በሌሎችም ስፖርቶች እንቅስቃሴዎችን በመጠለያ ጣቢያው እንዲያዘወትሩ ምክክር ማድረጋቸውም ተሰምቷል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...