Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የአገሪቱ የደን ሽፋን ከ15 በመቶ በላይ መሆኑን ደን ሚኒስቴር አስታወቀ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ሪፖርቱን ያሰማው የአካባቢና የደን ሚኒስቴር፣ የአገሪቱ የደን ሽፋን 15.5 በመቶ መሆኑን አስታውቋል፡፡

  የአካባቢና ደን ሚኒስትሩ አቶ በለጠ ታፈረ ባቀረቡት ሪፖርት ይፋ እንዳደረጉት፣ ባለፈው ዓመት በተጀመረውና በሳተላይት በታገዘው የደን ቆጠራ መሠረት የአገሪቱ የደን ሽፋን 15.5 በመቶ ደርሷል፡፡ ይሁንና የአገሪቱ ደን ሽፋን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሦስት በመቶ ብቻ እንደነበር ሲገለጽ ለዓመታት ቆይቷል፡፡ አካባቢ ጥበቃ አቀንቃኞች በበኩላቸው አገሪቱ የደን ሽፋን አሥር በመቶ መድረሱን ይህም፣ የዓለም የእርሻና የምግብ ድርጅት (ፋኦ) ያወጣቸውን የደን ቆጠራ ሥልቶች መሠረት በማድረግ እንደነበር ሲገልጹም አይዘነጋም፡፡

  የአገሪቱ የደን ሽፋን ቆጠራ አገር አቀፍ የደን ሀብት መረጃ ለማደራጀት ታስቦ የተጀመረ ሥራ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ደን ቆጠራው 17 በመቶ ደርሶ እንደነበርና በዚህ ዓመት መቶ በመቶ ቆጠራው ይካሄዳል ተብሎ ታቅዶ እንደበርም አቶ በለጠ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና እስካሁን ሊካሄድ የቻለው የደን ቆጠራ መጠን 41 በመቶ ብቻ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ የታሰበውን ያህል ሙሉ በሙሉ በአገሪቱ ያለውን ደን ለመቁጠር ያልተቻለው በቂ የትራንስፖርት አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት እንደሆነም ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡

  የደን ልማት ሥራዎችን ለማስፋፋት አንድ ቢሊዮን ብር ሊያስገኙ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የፋይናንስ ድጋፍ ለማፈላለግ በተደረገው እንቅስቃሴ መሠረት የተገኘው 14.1 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የገለጹት አቶ በለጠ፣ የኖርዌይ መንግሥት የ10.6 ሚሊዮን ዶላር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ፕሮግራም የ543 ሺሕ ዶላር፣ የዴንማርክ መንግሥት የአንድ ሚሊዮን ዶላር መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

  በሌላ በኩል ግማሽ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚገመቱ የአጠናና የቀርከሃ ደን ውጤቶችን በበጀት ዓመቱ ውስጥ ለገበያ ለማቅረብ ታስቦ እንደነበር፣ ከዚህ ውስጥ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለገበያ የቀረበው 175 ሺሕ ሜትር ኪዩብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ሆኖም የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት ዕቅድና የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ለአገር ውስጥ ገበያ ካቀረበው ደን ምርት ገቢ መገኘቱን አመላክተዋል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከ35,400 ሜትር ኪዩብ በላይ የደን ምርት አቅርቦ 53.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል ያሉት አቶ በለጠ፣ ከኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ የቀረበው 93,702 ሜትሪክ ቶን የደን ውጤትም 157.81 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ እንጨት ካልሆኑ ምርቶች የተገኘውን 7.6 ሚሊዮን ብር ጨምሮ በጠቅላላው 218.8 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል ብለዋል፡፡

  በዚህ ዓመት ለገበያ ይቀርባል የተባለው ግማሽ ሚሊዮን ኩንታል ዕጣንና ሙጫ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መታቀዱን፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥም 22,218.5 ኩንታል ለውጭ ገበያ መቅረቡንና ከ152.3 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን፣ ለአገር ውስጥ ገበያ ከቀረበ የተፈጥሮ ሙጫ ከ7.4 ሚሊዮን ብር በላይ በመገኘቱ፣ በጠቅላላው 160 ሚሊዮን ብር ያህል መገኘቱን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከ15 ሺሕ ሜትር ኪዩብ በላይ አጣናና ቀርከሃ ወደ ውጭ ተልኮም 39 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች