Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአቶ በቀለ ገርባ ለሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እታገላለሁ አሉ

  አቶ በቀለ ገርባ ለሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እታገላለሁ አሉ

  ቀን:

  አቶ በቀለ ገርባ በሌሎች አገሮች እንደሚታየው ዓይነት ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግርን በኢትዮጵያ ለማምጣት እታገላለሁ አሉ፡፡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ይህንን ያሉት ሪፖርተር ከእስር ከተፈቱ በኋላ ረቡዕ የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝቶ ባነጋገራቸው ወቅት ነበር፡፡

  ‹‹ምንም እንኳን እኔ ከእስር ብፈታም በርካቶች ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነት፣ ለብልጽግናና ለአገር አንድነት ዋጋ በመክፈል ሲጽፉ፣ ሲናገሩና ሲከራከሩ የነበሩ ሰዎች አሁንም ድረስ እስር ቤት ናቸው፡፡ ይህ ደስታዬ የተሟላ እንዳይሆን ያደርገዋል፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

  መንግሥት በሁለት ወራት ውስጥ እፈታቸዋለሁ ባለው መሠረት የፈታቸው እስረኞች ቁጥር እጅግ አናሳ ነው ያሉት አቶ በቀለ፣ ወደፊት ሕዝቡ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ፍትሐዊ ምርጫ መካሄድ እንዳለበትና ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  በአገሪቱ ፖለቲካም ያገባኛል የሚሉ በተለይ ‹‹እምብዛም ቦታ ያልተሰጣቸው›› ውጭ አገር ያሉ ኃይሎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው በፖለቲካው እንዲሳተፉ ጥሪ እንዲደረግም አሳስበዋል፡፡

  አቶ በቀለ ገርባ መፈታታቸውን አስመልክቶ አዳማ በሚገኘው በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ለተገኙ ደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በስፍራው በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው መገኘታቸውን ሪፖርተር ታዝቧል፡፡

  ትናንት ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር ከተፈቱት ስድስት ግለሰቦች በተጨማሪ ዛሬ ደግሞ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አመራር የነበረው አቶ አንዷለም አራጌ፣ አቶ አህመዲን ጀበል፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) እና አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች ተፈትተዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...