Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ዘው ብሎ ገባ]

  • ፈለከኝ?
  • ተቃውሞ እያቀረቡ ናቸው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እነማን ናቸው ተቃውሞ የሚያቀርቡት?
  • የውጭ ዲፕሎማቶች፡፡
  • ደግሞ ምን ሆኑ?
  • በጣም ጠበቀብን እያሉ ነው፡፡
  • ያስፉታ ታዲያ?
  • ምኑን?
  • ያጠበቃቸውን ነገር፡፡
  • ያጠበቃቸው የእኛ ፖሊሲ ነው፡፡
  • የትኛው ፖሊሲ?
  • የቢዝነስ ቪዛ ለማግኘት ያለው ፕሮሰስ በዛብን እያሉ ነው፡፡
  • ምን አልከኝ?
  • የቢዝነስ ቪዛ ለማግኘት ተቸገርን እያሉ ነው፡፡
  • ምን ይደረግልን ነው የሚሉት?
  • ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ብዙ እየተጉላሉ ነው፡፡
  • ታዲያ እንደፈለጉ ዘው ማለት አማራቸው?
  • እንደሱ እንኳን እያሉ አይደለም፡፡
  • የእኛ ዜጐች በጣም አይደለም እንዴ የሚቸገሩት?
  • ምን ለማድረግ?
  • የእነሱን ቪዛ ለማግኘት፡፡
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • ታዲያ የእነሱ ጠብቆ የእኛ ለምን ይላላል?
  • ያው እኛ እነሱን እንፈልጋቸዋለን፡፡
  • ለምንድን ነው የምንፈልጋቸው?
  • ለማደግ ነዋ፡፡
  • እነሱ እኛን አይፈልጉንም?
  • እነሱማ አድገዋል፡፡
  • ታዲያ ያደጉት በእኛ ዕርዳታ ነው?
  • ኧረ በፍጹም፡፡
  • ስለዚህ እኛም ለማደግ የእነሱን ዕርዳታ አንፈልግም፡፡
  • ይህ እንኳን ብዙ የሚያስኬደን አይመስለኝም፡፡
  • ለምን አያስኬደንም? ቻይና በዕርዳታ ነው ያደገችው?
  • አይደለም፡፡
  • አሜሪካስ ብትሆን በማን ዕርዳታ ነው እዚህ የደረሰችው?
  • እሱማ በራሷ ጥረት ነው፡፡
  • እኛም በራሳችን ጥረት ማደግ እንችላለን፡፡
  • ምን እያሉ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • የአገራችን ባለሀብቶች ላይ ነው ትኩረት ማድረግ ያለብን፡፡
  • አሁን እኮ የምንኖረው ግሎባላይዝድ በሆነች ዓለም ላይ ነው፡፡
  • ለምን ማርስ ላይ አንኖርም? ማደግ እንችላለን እንችላለን፡፡
  • ዕድገት እኮ በፉከራ አይመጣም፡፡
  • የምን ፉገራ ነው? እኔ ነኝ ፎጋሪው?
  • በፉገራ ሳይሆን በፉከራ ነው ያልኩት፡፡
  • ብቻ በፉከራም ቢሆን በፉገራ ማደጋችን አይቀርም፡፡
  • ለማንኛውም ብናስብበት ጥሩ ነው፡፡
  • ምንም የምናስብበት ነገር የለም፡፡
  • እ…
  • እነሱም ሉዓላዊ አገር እኛም ሉዓላዊ አገር፤ በቃ፡፡
  • እሺ እንዳሉ፡፡
  • ጨርሻለሁ፡፡

   

  [የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ የተለያዩ ወረቀቶች ይዛ ገባች]

  • ምንድን ነው ይዘሽ የመጣሽብኝ?
  • ደብዳቤዎችና የጥሪ ወረቀት ነው፡፡
  • የምን የጥሪ ወረቀት ነው?
  • አንድ ግብዣ አለ፡፡
  • የምን ግብዣ ነው?
  • የአንድ አርቲስት ልደት ይከበራል፡፡
  • የት?
  • እዚያ ትልቁ ሆቴል፡፡
  • እና እኔ ምን አደርጋለሁ?
  • ምን ማለት ነው ምን አደርጋለሁ?
  • እኮ እኔ ምን አደርጋለሁ?
  • ግብዣው ላይ ይገኛሉዋ፡፡
  • ማን? እኔ?
  • አዎና፡፡
  • ሥራ አጥቼ ነው?
  • ይኼ እኮ ሥራ አይደለም መዝናኛ ነው፡፡
  • እኔ ብዙ ሥራ ስላለብኝ አልገኝም፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር በርካታ ባለሥልጣናት እኮ ይገኛሉ፡፡
  • ለምን?
  • የአርቲስቱን ልደት ሊያከብሩ ነዋ፡፡
  • ሥራ የላቸውም እንዴ?
  • ይኼ እኮ ሥራ አይደለም መዝናኛ ነው አልኩዎት፡፡
  • ታዲያ በሌላ ነገር አይዝናኑም?
  • ታዋቂ ሰው ነው፡፡
  • ማን?
  • ጋባዡ፡፡
  • እኔ ከታዋቂ ይልቅ አዋቂ ሰው ይሻለኛል፡፡
  • እና አይገኙም?
  • ኧረ አላበድኩም፡፡
  • እንዳይቀየምዎት ግን፡፡
  • በቃ ጥሩ ምክንያት ፈልጊልኝ፡፡
  • የምን ምክንያት?
  • የምቀርበት፡፡

  [የክቡር ሚኒስትሩ ጓደኛ ሚኒስትር ደወሉ]

  • መቼም ክቡር ሚኒስትር ደርስዎታል?
  • ምኑ?
  • ግብዣው፡፡
  • የቱ ግብዣ?
  • የአርቲስቱ ልደት፡፡
  • አዎን ደርሶኛል፡፡
  • እንገናኛለና?
  • ትሄዳለህ ማለት ነው?
  • መጠየቁስ፡፡
  • እ…
  • ልንምነሸነሽ እኮ ነው፡፡
  • በምን?
  • በብር፡፡
  • ምን አልከኝ?
  • ሊያልፍልን ነው በቃ፡፡
  • እንዳያልፍብህ ተጠንቀቅ፡፡
  • እ…
  • የራስህንም፣ የመንግሥትንም፣ የአገርህንም ክብር ጠብቅ፡፡
  • ብር ካለ፣ ክብር አለ፡፡
  • ውርደትም አለ፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • ብቻ ተጠንቀቅ፡፡
  • እና አይመጡም ክቡር ሚኒስትር?
  • ለምትሄዱትም አዝናለሁ፡፡
  • በሉ ይቅናህ በሉኝ፡፡
  • ምን ይቀናሃል ይንቅሃል እንጂ?

  [የክቡር ሚኒስትሩ አንድ ወዳጅ ስልክ ደወለላቸው]

  • ምን እየሠራችሁ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ብዙ ሥራ ነው የምንሠራው?
  • ምን እየተሠራ እንደሆነ አልገባኝም?
  • ምን ተሠራ?
  • አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት፡፡
  • ጠይቀኝ፡፡
  • ባለፈው ምርጫውን ማሸነፋችሁን ስትነግሩን ያልመረጠንንም እናገለግላለን ስትሉ አልነበር እንዴ?
  • ብለናል፡፡
  • በአገሪቱ የሕጐች ሁሉ የበላይ የቱ ነው?
  • ሕገ መንግሥቱ ነዋ፡፡
  • ይኸው አንዱ ወዳጄ ሕገ መንግሥታዊ መብቱን ሲፈጽም ታሰረ፡፡
  • ምን አድርጐ?
  • ለምን ምርጫው የተበላ ዕቁብ ነው አልክ? ተብሎ ታሰረ፡፡
  • ምርጫውማ የተበላ ዕቁብ አለመሆኑን ሕዝብ በራሱ ድምፅ አረጋግጧል፡፡
  • ታዲያ የእሱ መናገር ውጤቱን ይቀይረዋል?
  • አይቀይረውም፤ ሊቀይረውም አይችልም፡፡
  • ይኸው ይህን ተናገርክ ተብሎ ዘብጥያ ወርዷል፡፡
  • ይኼማ ትክክል አይደለም፤ መሆንም የለበትም፡፡
  • ግን ሆኗል፡፡
  • እስቲ አጣራለሁ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በኢኮኖሚ ያስገኛችሁትን ዕድገት በሌላውም ልትደግሙት ያሻል፡፡
  • በሌላ በምን?
  • በመልካም አስተዳደር፣ በሰብዓዊ መብት፣ በሙስናና በሌላም፡፡
  • ይኸው ወገባችንን ታጥቀን እየሠራን ነው፡፡
  • ወገባችሁ ላይ ያሉትን ሞላጮች ግን አራግፉ፡፡
  • ሁሌም ሕዝባችንን ለማገልገል ጠንክረን እንሠራለን፡፡
  • የምትሰብኩትን ግን ኑሩት፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ ማታ ቤት ገብተው ከሚስታቸው ጋር ቴሌቪዥን እየተመለከቱ ነው፡፡ የአርቲስቱ የልደት ፕሮግራም በቀጥታ እየተላለፈ ነው]

  • አልተጠራህም እንዴ?
  • ተጠርቼ ነበር፡፡
  • ታዲያ ለምን አልሄድክም?
  • ማን? እኔ?
  • የማወራው አንተን አይደለም እንዴ?
  • እኔ እኮ የአገር መሪ ነኝ፡፡
  • ታዲያ ብትሆንስ?
  • ብዙ ሥራ አለብኝ፡፡
  • ይኼ ሥራ ሳይሆን መዝናኛ ነው፡፡
  • ኦ ሴትዮ በቃ እኔን አይመጥነኝም፡፡
  • ታዲያ እኔ ለምን አልሄድም ነበር?
  • ኪራይ ሰብሳቢ ሆነሻል ልበል?
  • የማይገኝ አጋጣሚ ነው ብዬ ነው፡፡
  • ኪራይ ለመሰብሰብ?
  • ያው ብዙ ባለሥልጣን አይደል እንዴ የተገኘው?
  • አፍሬያለሁ እባክሽ፡፡

  [የክቡር ሚኒስትሩ ጓደኛ ሚኒስትር ደወሉ]

  • ቀጠሮ ነበረን እኮ ክቡር ሚኒስትር?
  • የት?
  • ግብዣው ቦታ ነዋ፡፡
  • ይኸው በቴሌቪዥን እያየኋችሁ ነው፡፡
  • አልመጣሁም እያሉኝ ነው?
  • እናንተም በመሄዳችሁ አፍሬያለሁ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እንደዚህ ዓይነት ግብዣዎች እኮ የግሉና የፐብሊክ ሴክተሩን የሚያስተሳስሩ ናቸው፡፡
  • በምንድን ነው የሚያስተሳስሩት?
  • እ…
  • አገር የሚጠቅም ፕሮግራም ላይ ተገኙ ስትባሉ አትገኙም፤ እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራም ላይ ግን ለመገኘት የሚቀድማችሁ የለም፡፡
  • ይኼም ቢሆን ለአገር ይጠቅማል፡፡
  • ይኼ ለአገር ሳይሆን ለእናንተ ነው የሚጠቅመው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ሆደ ሰፊ መሆን አለብዎት፡፡
  • እናንተ ሆደ ሰፊ ብቻ አይደላችሁም፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነን?
  • ሆዳሞች!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...

  አዲስ አበባ እንዳይገቡ በተከለከሉ ዜጎች ጉዳይ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተወያይተው ችግሩ እንዲፈታ አደረጉ

  ለሳምንታት በርካታ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረውና ከአማራ ክልል በደብረ ብርሃን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...