Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናኢትዮጵያና ኡጋንዳ ስምምነቶቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መከሩ

  ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ስምምነቶቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መከሩ

  ቀን:

  በኡጋንዳ የመከላከያ ሚኒስትር የተመራው የልዑካን ቡድን በቅርቡ በኢትዮጵያ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ከመመለሱ በፊት፣ ሦስት ተጨማሪ ስምምነቶች ተፈራረመ፡፡ ሁለቱ አገሮች ያደረጉዋቸው ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ መርሐ ግብር ለመቅረፅ መክረዋል፡፡

  ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ቀደም ሲል በመሠረተ ልማት ዝርጋታና በደኅንነት ላይ በርካታ ስምምነቶች የተፈራረሙ ሲሆን፣ አሁን ተግባራዊ ለማድረግ መክረዋል፡፡ በግብርና፣ በትምህርትና በቱሪዝም ዙሪያዎች ተጨማሪ ሦስት ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡

  በርከት ያሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በግዮን ሆቴል በተካሄደው ምክክር የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ሲዳሰስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ‹‹ከጥንት ጀምሮ ሁለቱ አገሮች እህትማማች ሆነው የቆዩ ናቸው፡፡ አንድ ተፋሰስ፣ ተመሳሳይ ቋንቋና ባህል ይጋራሉ፤›› ብለዋል፡፡

  የሁለቱ አገሮች የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ሲጠናቀቅ ዶ/ር ቴድሮስ ከኡጋንዳ የመከላከያ ሚኒስትር ክሪስፐስ ክያንጎ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ከወንድሜ ቃላት ልዋስና አሁን የሚቀረን ወደ ተግባር መግባት ነው፡፡ ስምምነቶቹን ለማሳካት ቁጥር አንድ ትግበራ፣ ቁጥር ሁለት ትግበራ፣ ቁጥር ሦስት ትግበራ ብቻ ነው፤›› ብለዋል፡፡

  በኢጋድ አማካይነት በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና በተለይ ደግሞ በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ የኡጋንዳ የመከላከያ ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አገሬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ጠንካራ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ ትሰጠዋለች፤›› በማለት፡፡

  ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ በርካታ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችም አሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...