የመጻሕፍት ምርቃት
ዝግጅት፡‑ ‹‹ዶ/ር አይቮሊክ›› የተሰኘው የኮርኔይ ሹኮቨስኪ የሕፃናት መጽሐፍና ‹‹ቫክሳ ክሊያክሳ›› የተሰኘው የሳሙኤል ማርሻክ የሕፃናት መጽሐፍ ከራሺያኛ ወደ አማርኛ በዶ/ር ንጉሤ ካሳዬ ወልደ ሚካኤል ተተርጉመዋል፡፡ በይፋ ከተመረቁ በኋላ በሩሶኪምየር ፋውንዴሽን ድጋፍ በትምህርት ቤቶች በነፃ ይከፋፈላሉ፡፡
ቀን፡‑ ሐምሌ 24 ቀን 2007 ዓ.ም.
ሰዓት፡‑ 11፡30
ቦታ፡‑ የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል አዳራሽ
አዘጋጅ፡‑ የሩሲያ ሳይንስና የባህል ማዕከል
ውይይት
ዝግጅት፡‑ ‹‹ዶ/ር አሸብር›› በተሰኘው የአሌክስ አብርሃም መጽሐፍ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ ዓለማየሁ ገላጋይ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሐሳቦችን ያቀርባል፡፡
ቀን፡‑ ሐምሌ 26
ሰዓት፡‑ 8፡00
ቦታ፡‑ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር)
አዘጋጆች፡‑ እናት ማስታወቂያ፣ ጐተ ኢንስቲትዩትና ወመዘክር