Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየተጠናቀቀው የ10 ሚሊዮን ዶላር የወባ ፕሮጀክት

  የተጠናቀቀው የ10 ሚሊዮን ዶላር የወባ ፕሮጀክት

  ቀን:

  የኢትዮጵያን የጤና ተቋማት ዓይነት የመለየት፣ ምርመራ የማካሄድና የማከም አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረውና አሥር ሚሊዮን ዶላር የወጣበት የዘጠኝ ዓመት መርሐ ግብርን መጠናቀቁን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

  ከጥቅምት 2000 ዓ.ም. እስከ የካቲት 2010 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ይኸው ፕሮጀክት ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል ከ3,500 በላይ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች አስተማማኝ የማይክሮስኮፕ አጠቃቀም እንዲሁም 2,400 የጤና ክብካቤ ባለሙያዎች ለወባ በሽተኞች የተሻለ ሕክምና መስጠት የሚያስችላቸው እንዲሠለጥኑ ማድረግ ተችሏል፡፡

  ከዚህ ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ከ100 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሻሻላቸው ከስኬቶቹ መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡

  ፕሮጀክቱ የተተገበረው በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅትና በአሜሪካ መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል የሚመራው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የወባ መርሐ ግብር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው፡፡

  ከሁለት ሦስተኛ በላይ ሕዝቧ በከፍተኛ ሁኔታ ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩባትና በየዓመቱ 1.5 ሚሊዮን የወባ በሽታ ክስተቶች በሚመዘገቡባት ኢትዮጵያ ወባ ቀዳሚው የጤና ሥጋት ነው፡፡ ለክስተቶች ትክክለኛና አፋጣኝ ምርመራና ሕክምና ማድረግ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዋነኛው መንገድ ነው፡፡

  ባለፈው አሠርት ኢትዮጵያ የወባ በሽታን በመዋጋት አስደናቂ ውጤት እንዳስመዘገበች፣ በ2003 ዓ.ም. 59 በመቶ የነበረው በሽታውን በአስተማማኝ ሁኔታ በላቦራቶሪ የመለየት አቅም፣ በ2008 ዓ.ም. ወደ 97 በመቶ ከፍ እንዳለ ይህም ከወባ በሽታ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሞት መጠንን በእጅጉ እንደቀነሰ ኤምባሲው አመልክቶ፣ በ2004 ዓ.ም. 2000 ደርሶ የነበረው የሟቾች ቁጥርም በ2009 ዓ.ም. ወደ 374 ዝቅ እንዳለ አስረድቷል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...