Thursday, August 11, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ፌርማታ ፅሁፎች

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሐጂና ኡምራ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ከነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማጓጓዝ ጀመረ

  ትኩስ ፅሁፎች

   አየር መንገዱ በመጪዎቹ 24 ቀናት 6,000 መንፈሳዊ ተጓዦች እንደሚያጓጉዝ አስታውቆ፣ ለዚሁ ተልኮ ቦይንግ 787 ድሪምላይነርና ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን እንደመደበ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ፎቶግራፍ፡- ታምራት ጌታቸው

  *************

  ያንድ አዝማሪ ዘፈን

  ‹‹አንቺን አይቼ፣

  ‹‹አንቺን በአእምሮዬ ፀንሼ፣

  ‹‹እንደመንፈስ በልቦናዬ ሠርፀሽ ስትከሰች፣

  ‹‹ልቤ ማኅደር ሁኖ ለኅብረ ቀለምሽ ሳስቶ፣

  ‹‹በስስ ልቤ ውስጥ ረቂቅ ፍቅር ተንሠራፍቶ፣

  ‹‹መንፈሴ በነፃነት ታብቶ፣ ሥጋዬም መሬትን ሊለቅ ተነሥቶ፤

  ‹‹በእንዲህ ሁኔታ በጨረቃ ተመልክቶ፤

  (በጨቅላ ዘመኔ ስለማለት)

  ‹‹በልቡናዬ – በልቤ – በሠራ አካላቴ፤

  ‹‹ልወድሽ ነበር ቃል ገብቼ፤ አፍታ ሳልል ደቂቃ፡፡

  ‹‹ታዲያ – ድንገት ታዲያ ፀሐይ ሠርቃ፣

  ‹‹ዐይኔ ተከፍቶ የኅሊና የተኛ ልቤ ቢነቃ፣

  ‹‹ፀሐይ – ፀሐይ ቃጠሎ ያደበዘዘው መልክሽ፣

  ‹‹በጨረቃማው ምሽት ትናንት ያየሁት ኅብርሽ፤

  ‹‹ቀለም ብቻ ሆነብኝ የተለያየ፤

  ‹‹አርማሽ እንደዐረም ተኮሽልሎ፤

  ‹‹ጨርቅ ብቻ ሆንሽብኝ

  ‹‹ንፋስ በጥፊ የሚመታሽ፤

  ‹‹ሳይሽ ዛሬን በፀሐይ

  (በውርዝውና ዘመኔ እንደማለት)

  ‹‹ዛሬን ላይሽ-በንፋስ ውስጥ ባየር ብቻ ስትረግቢ፡፡

  ‹‹‹ሳይሽ ዛሬን ትኩር ብዬ በፀሐዩ-

  ‹‹ሳይሆን በደመና –

  ‹‹መንፈሴ ሸፈተ መና ሆንሽበትና፤

  ‹‹ዛሬን ሳይሽ አተኩሬ፣

  ‹‹በፀሐዩ በጠራራ፤

  ‹‹አይ አንቺ ባንዲራ የወዲያዋ

  ‹‹ተውለብላቢ ጨርቅ የዛሬዋ!››

  • ዮናስ አድማሱ ‹‹ጉራማይሌ›› (2006)

  *************

  ልዩ

  እየደገፍካቸው የሚያዘነብሉት

  እየጠገንካቸው የሚፈራርሱት

        ለምን ይመስልሃል?

  እየቀባሃቸው አመዳቸው ቦኗል

  እያጎረስካቸው አጥንታቸው ቆሟል

        ለምን ይመስልሃል?

  እኔ እነግርሃለሁ እውነቱን

        ምስጢሩን

  ያንተ ረዳትነት ከሰው መለየቱን…

  አንድ እጅህ ሲደግፍ … ሌላኛው ይገፋል

  ሐሳብህ ሲጠግን ተግባርህ ያፈርሳል

  ከላይ እየቀባህ ከታች ትጠርጋለህ

  ፈትፍተህ አጉርሰህ

  ወደ ጉሮሯቸው ጣትክን ትሰዳለህ

  በማስመለሳቸው አዝነህ ትታያለህ

  ወዳጄ ልንገርህ?

  አንተ ትለያለህ፡፡

  *****************

  4ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ መጋቢት፣ 2006

  ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ባስቆጠረው የኦሎምፒክ ጉዞ በርካታ ስፖርቶች ያለ ሴቶች ተሳትፎ ተደርገዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሴቶች ተካፋይ የነበሩባቸው ስፖርቶች በዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የመሰረዝ አደጋ አጋጥሟቸውም ነበር፡፡ ሴቶች እንዲሳተፉ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ከመወሰኑ በፊት አብዝተው የሚካፈሉባቸው ስፖርቶች ኔትቦል እየባሉ የሚጠሩትንና የብስክሌት ውድድሮችን ያካተቱ ውድድሮች ብቻ ነበሩ፡፡ የገና ጨዋታ እ.ኤ.አ. ከ1908 በፊት ሴቶችን ሲያወዳድር ቢቆይም በድጋሚ በኦሎምፒክ መድረክ ተሳትፎአቸውን እንዲያገኙ የተፈቀደው እ.ኤ.አ. ከ1980 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡

  እ.ኤ.አ. በ1992 በተደረገው የባርሴሎና ኦሎምፒክ ወንዶች በ159 ፆታዎች እንዲወዳደሩባቸው የተደረጉ ስፖርቶች ደግሞ 12 ነበሩ፡፡ በፈረንዶቹ ሚሌኒየም ሲድኒ ባስተናገደችው ኦሎምፒክ ቦክስ ነፃ ትግልና የቤዝ ቦል ጨዋታዎች የተፈቀዱት ለወንዶች ብቻ ነበር፡፡

  በኦሎምፒክ የሴቶች የተሳትፎ ቁጥር ማነስ ዓለም አቀፉን የኦሎምፒክ ኮሚቴ አዘውትሮ በአጀንዳነት የሚያወያይ ዓብይ ጉዳይ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በየአገራቱና በየክፍለ ዓለማቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንስቶች የሚያዘወትሯቸው እንደ ቅርጫት ኳስ፣ የገና ጨዋታ፣ እግር ኳስና ቫሊቮል የመሳሰሉ ስፖርቶች ቢኖሩም በኦሎምፒክ መድረክ ይፋ የሴቶች ውድድር ሆነው ብቅ ያሉት ግን በግዜ ሒደት ነበር፡፡ የሴቶች የኦሎምፒክ ተሳትፎ እስከ ለንደን 2012 ድረስ 50 በመቶ እንኳን መድረስ አልቻለም ነበር፡፡ ነገር ግን ባለፈው ግማሽ ዓመት ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል ማለት ይቻላል፡፡ እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ አሥር በመቶ የነበረው የሴቶች ተሳትፎ በ2012 45 በመቶ ደርሷል፡፡

  ***************

  ከአስገራሚ የባሕር ላይ ጥቃቶች መካከል

  • እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 1992 ዓ.ም. ጠላፊዎች ማላካ እስትሪት በሚባለው ቦታ ናጋሳኪ እስፕት የተባለችውን የጃፓን ነዳጅ ጫኝ መርከብ ይጠልፋሉ፡፡ መርከቧን አውሮማቲክ ፓይለት ላይ በሙሉ ፍጥነቷ አድርገው የመርከቧን ካፒቴን (Ship’s Master) ለመደራደሪያነት ይዘው ከመርከቧ ይወርዳሉ፡፡

  መርከቧ ላይ ያለ ካፒቴን /አውቶማቲክ ፓይለት/ በሙሉ ፍጥነቷ ባሕሩን እየሰነጠቀች ትጓዝና አሽንብሊሲንግ ከተባለች ኮንቴይነር ጫኝ መርከብ ጋር ትጋጫለች፡፡ ግጭቱን ተከትሎ በተነሳው እሳት የአሸን ብለሲንግ መርከብ ባሕረኞች በሙሉ ሲሞቱ ከናጋሳኪ እስፕት ሁለት ሰዎች ብቻ ተርፈዋል፡፡ ኦሸን ብለሲንግም ለስድስት ሳምንታት ያህል በቆየ እሳት ተበልታለች፡፡

  • በጥቅም 1985 እ.ኤ.አ. አቺል ላውሮ የተባለች የመንገደኞች መርከብ በግብፅ ባሕር ጠረፍ አካባቢ ከፍልስጤም ነፃ አውጪ ግንባር (PLO) ወገን ነን ባሉ ጠላፊዎች ታገተች፡፡ አጋቾቹም እስራኤል የያዘቻቸውንና በእስር ላይ ያሉ የ(PLO) አባላት እንዲፈቱ ጠየቁ፡፡ እስራኤልም ጥያቄውን ለመመለስ አሻፈረኝ በማለቷ አጋቾቹ እስራኤላዊ አሜሪካዊ የሆነውን ሊዮን ክሊንግሆፈር የተባለ ቱሪስት ገድለው ሬሳውን ወደ ባሕር ጣሉ፡፡
  • የባሕር ወንበዴዎች እ.ኤ.አ. በ2003 ዓ.ም. ማላካ እስትሬት አካባቢ ዳዊ ማድራም የተባለች ነዳጅ ጫኝ መርከብ አገቱ፡፡ በወቅቱ ዘኢኮኖሚስትን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን የአጋቾቹ ዓላማ የመርከቧን (የባሕረኞችን) ንብረት መዝረፍ ሳይሆን የመርከብ አነዳድ ለመማርና ስለ መርከብ የሚያስረዱ ማንዋሎችንና ቴክኒካል መረጃ የያዙ ሰነዶችን ለመስረቅ መሆኑ ቢጠቀስም ዓለም አቀፍ የባሕር ጉዳይ ድርጅት (In’t Maritime Organization) መገናኛ ብዙኃን የዘገቡትን የጠለፋ ዓላማ የተሳሳተና ተረትተረት ነው ብሎታል፡፡

  ማሪታይም ጆርናል፤ 2002 ዓ.ም.

   

   

  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ተጨማሪ ለማንበብ

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች