Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኢሕአዴግ አጋር በሆነው በአፋሩ አብዴፓ አመራሮች መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ

  የኢሕአዴግ አጋር በሆነው በአፋሩ አብዴፓ አመራሮች መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ

  ቀን:

  የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አጋር የሆነው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ፡፡ በዚህ ምክንያት የክልሉን ቋሚ መስተዳድር መመሥረት እንዳልተቻለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

  አለመግባባቱ የተፈጠረው አብዴፓንና የአፋር ክልልን ላለፉት 20 ዓመታት ሲመሩ በቆዩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድንና እሳቸውን ተክተው በተመረጡት የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ ቡድን መካከል መሆኑን፣ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ የክልሉ መንግሥት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፣ በሌሎች ክልላዊ መንግሥቶች የሥልጣን አወቃቀር መሠረት የፓርቲው ሊቀመንበር እንደመሆናቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርም ሊሆኑ ይገባል የሚል ክርክር፣ በአቶ ጠሃ ቡድን አማካይነት መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

  ይህ ጥያቄ ግን አብላጫ ድምፅ ባለው የአቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድን በኩል ተቀባይነት ማግኘት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  በዚህ ምክንያት አቶ ጠሃ መሐመድና አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሌሉበት የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ከአንድ ወር በፊት ተካሂዶ፣ አቶ እስማኤል ለተጨማሪ ሦስት ወራት በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት እንዲቆዩ፣ ካልሆነ ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ጊዜያዊ አስተዳደር ይመሥርት በሚለው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በስተመጨረሻም ከክልሉ ምክር ቤት ውጪ ሥራ አስፈጻሚው ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት መሾሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  በዚሁ መሠረት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የውኃ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አወል አርባ፣ በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ለሦስት ወራት መመረጣቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በወደፊቱ ጉዳይ ላይ መግባባት ባለመቻሉ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እየመከረ እንደነበር፣ በዚህ ስብሰባ ላይም የኢሕአዴግ ተወካዮች ለታዛቢነትና ለማስታረቅ መገኘታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

  በትጥቅ ትግሉ ወቅት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሕወሓት አባል የነበሩ ሲሆን፣ በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ የአፋር ክልል ተወላጅ ናቸው፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የአብዴፓ ሊቀመንበር በመሆን ለ20 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

  በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ክልሉን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠዋል፡፡    

  በአብዴፓ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና እየተካሄደ ስለነበረው ድርድርና ምክክር ለአብዴፓ ጽሕፈት ቤት፣ለክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ለኢሕአዴግ የውጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...