Tuesday, August 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበመንገድ ንብረቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት መባባሱ ተገለጸ

  በመንገድ ንብረቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት መባባሱ ተገለጸ

  ቀን:

  በአዲስ አበባ ከተማ በመንገድ ንብረቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳትና ሕገወጥ ተግባር እየተባባሰ መምጣቱ አሳሳቢ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ በመንገድ ንብረቶች ላይ በ2007 ዓ.ም. የደረሱ ጉዳቶችና ሕገወጥ ተግባራት ከ2006 ዓ.ም. ሲነፃፀሩ ልቀው ተገኝተዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ የመንገዶች ባለሥልጣን የመንገድ መብት ጥበቃና አስተዳደር ንዑስ የሥራ ሒደት መሪ አቶ አስመላሽ ኪዳነ ማርያም እንደገለጹት፣ በ2007 በጀት ዓመት ብቻ 569 በሚሆኑ የመንገድ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከጠቅላላ ጉዳቶቹ ውስጥ 244 በቀለበት መንገድ ላይ 325 ደግሞ ከቀለበት መንገዱ ውጭ ባሉ የከተማው መንገዶች ላይ ነው፡፡

  በተሽከርካሪዎች ግጭት፣ በስርቆትና በመሳሰሉት ተግባራት ጉዳት የደረሰባቸው ንብረቶች ግምት 5.34 ሚሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች ዋጋ ለማስመለስ የተቻለ ቢሆንም፣ የጉዳቱ መጠን በየዓመቱ እየጨመረ መሄዱ ግን አሳሳቢ መሆኑን አቶ አስመላሽ ተናግረዋል፡፡

  በ2006 ዓ.ም. በተመሳሳይ ወቅት በመንገድ ንብረቶች ላይ የደረሰው ጉዳት 406፣ የጉዳቱ መጠንም 2.48 ሚሊዮን ብር እንደነበር ያስታወሱት አቶ አስመላሽ፣ በ2007 ዓ.ም. ጉዳት በ162 ሊበልጥ መቻሉንና ጉዳት የደረሰበባቸው ንብረቶች ዋጋ መጠንም በእጥፍ መጨመሩን አስረድተዋል፡፡

  በባለሥልጣኑ ኃላፊነት መሠረት ቁጥጥር ከሚደረግባቸው መካከል የመንገድ አጥር፣ የኤሌክትሪክ ፖል፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ክዳኖችና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የትራፊክ ምልክቶች፣ የእግረኛ መለያ አጥሮችና የመሳሰሉት ንብረቶች ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስባቸው ንብረቶች ናቸው ተብሏል፡፡

  በሕገወጥ መንገድ በሚፈጸም ድርጊት ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ መኪናን በጐዳናዎች ላይ በማቆም ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ ለመከላከል በ2007 ዓ.ም. ብቻ 2,064 አሽከርካሪዎችን መቀጣታቸው ተገልጿል፡፡ መንገድ ላይ ለረዥም ጊዜ መኪና ማቆም ከመኪናው የሚፈሰው ዘይትና ቅባት ለመንገድ መበላሸት ምክንያት በመሆኑ፣ ለረዥም ሰዓት መኪና ማቆም የሚያስቀጣ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

  ለመንገድ መበላሸት ምክንያት የሆኑ የመንገድ ዳር የመኪና እጥበትን ለመቆጣጠርም በተሠራ ሥራ፣ በ2,340 መኪና አጣቢዎች ላይ ዕርምጃ ተወስዷል ተብሏል፡፡

  መንገድ በመቆፈርና የኤሌክትሪክ ፖሎች ላይ ማስታወቂያ የሰቀሉ 1,980 ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ስለተወሰደው ዕርምጃ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ድርጊቱ እየተስፋፋ መምጣቱን የገለጹት አቶ አስመላሽ፣ በ2008 በጀት ዓመት ቁጥጥሩን ለማጠናከር ባለሥልጣኑ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመንገድ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ሆን ተብለው የሚፈጸሙ ናቸውም በማለት አስረድተዋል፡፡

  መንገድን በመዝጋት የግንባታ ቁሳቁሶች የሚያፈሱት ይህንን ከማድረጋቸው በፊት በቅድሚያ ለሚደርሰው የመንገድ ጉዳት ክፍያ እንዲከፍሉ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሚያፈሱት ላይም በተመሳሳይ ዕርምጃ እየተወሰደም እንደሆነ ተገልጿል፡፡     

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

  ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ የአገሪቱ...

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...