Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ላይ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

  በክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ላይ ባለሥልጣናት ጣልቃ እንደሚገቡ ተጠቆመ

  ቀን:

  በክልል የመንግሥት ተቋማትና ሕዝብ ላይ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል የተቋቋሙ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች፣ የክልል ባለሥልጣናት ጣልቃ በመግባት ለሥራቸው እንቅፋት እንደሚሆኑ ተገለጸ፡፡

  የአገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት የሁለት በጀት ዓመት (የ2006 እና 2007) የፀረ ሙስና እንቅስቃሴን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው፣ የክልሎች የሥነ ምግባረና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ከፌዴራሉ የተለየ የሥራ አፈጻጸም እንዳለቸው ተነግሯል፡፡

  የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን እንደተናገሩት፣ የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚከታተላቸው ትልልቅና ግዙፍ የሕዝብ ሀብትን የሚያንቀሳቅሱ ድርጅቶችን ነው፡፡ በእነሱ ላይ ችግር ሲያጋጥም ኮሚሽኑ ለሚወስደው ዕርምጃ በትልልቅ ባለሥልጣናት ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙ ጥሩ ሲሆንም የማበረታታት ሁኔታዎች መኖራቸውን፣ ነገር ግን ክልሎች ተፅዕኖ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣናት ጣልቃ እየገቡ የምርመራ ሒደቶችን እንደሚያስቀሩም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ የጣልቃ ገብነቱን ዓይነትና ዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

  በፌዴራል በኩል ባለፉት ሁለት የበጀት ዓመታት በርካታ የሕዝብና የመንግሥት ንብረቶችን ማስመለስ መቻሉን፣ በሙሰኞች ተወስደው የነበሩ ንብረቶች መመለሳቸውንና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

  ሙስናን ለመከላከል የሚበተኑ ፖስተሮች፣ በመገናኛ ብዙኃን የሚነገሩና የሚታዩ ፖስተሮችና ድራማዎች ከማስተማር ባለፈ በተቃራኒው መልዕክት ስለማስተላለፋቸው የተነሳውን ጥያቄ ኮሚሽነር ዓሊ አልፈውታል፡፡

  በውይይቱ ላይ በቅርቡ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሆነው የተሾሙትና የጥምረቱ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ ሙስናን ለመከላከል በተለይ በምርመራ ጋዜጠኝነት ዙሪያ ቢሠራ የተሻለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሕክምና ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሙስና እየተፈጸመ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ቢገልጹም፣ ማብራርያ ሳይሰጥበት በዝምታ ታልፏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...