Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የኢትዮጵያ ባንኮች ከአፍሪካ ምርጥ 200 ባንኮች ተርታ እየተሠለፉ ነው

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  – ንግድ ባንክ ሲመራ እነ አዋሽ ይከተላሉ

  የአፍሪካ የባንኮችን የሀብት መጠን እየተነተኑ ደረጃ የሚሰጡ መጽሔቶች በየጊዜው በሚያወጧቸው ደረጃዎች ውስጥ መካተት ከጀመሩት ባንኮች መካከል ቀዳሚውን ሥፍራ በመያዝ ከኢትዮጵያ ትልቁን ደረጃ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል፡፡

  ዘ አፍሪካ ሪፖርት የተሰኘውና ዋና መሥሪያ ቤቱን በፈረንሣይ በማድረግ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚጽፈው መጽሔት በዚህ ወር ዕትሙ ከአፍሪካ ቀዳሚ 200 በማለት ደረጃ ካወጣላቸው ባንኮች ውስጥ ንግድ ባንክ ባካበተው የሀብት መጠን 23ኛው ለመሆን ችሏል፡፡

  በምሥራቅ አፍሪካ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው መስክ እየጎላ የመጣው ንግድ ባንክ፣ በአፍሪካ ሪፖርት ከትልልቅ ጎራ እንዲሠለፍ የቻለው ከ11.8 ቢሊዮን ዶላር ወይም 236 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ሀብት በማፍራቱ ነው፡፡ ይሁንና የባንኩ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግን ሀብቱ ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ280 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ነው፡፡ መጽሔቱ የንግድ ባንክ ደረጃ ውጤትን እ.ኤ.አ. የ2015 ብቻ ያለውን በመጠቀም ያሳየ ሲሆን፣ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና ዳሸን ባንክም በደረጃ ሰንጠረዡ ከተካተቱት የኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ ይገኙበታል፡፡

  አዋሽ ባንክ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ሀብት በማስመዝገብ 163ኛ ደረጃን ሊይዝ ችሏል፡፡ ይሁንና አምና ከነበረው ደረጃ በአምስት መቀነሱንም የመጽሔቱ አኃዝ ይጠቁማል፡፡ ከአዋሽ ባንክ ቀጥሎ በ164ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ዳሸን ባንክም በተመሳሳኝ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያስመዘገበ ኢትዮጵያዊ ባንክ ሆኗል፡፡ ዳሸን አምና ከነበረው ደረጃ በእጅጉ ያሽቆለቆለው 13 ደረጃዎችን ወደ ታች በመቀነስ እንደሆነም የመጽሔቱ ሰንጠረዥ አስፍሯል፡፡

  እንደ ስታንዳርድ ባንክ ያሉ የደቡብ አፍሪካ ባንኮች አብዛኛውን ከፍተኛ ደረጃ በያዙበት በዚህ የደረጃ አሰጣጥ ላይ የተሳተፉት 200 ቀዳሚ ባንኮች የተመረጡት ዝርዝር መጠይቅ ተልኮላቸው ከተወዳደሩ 900 የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ተመርጠው እንደሆነ መጽሔቱ አስፍሯል፡፡

  አፍሪካን ቢዝነስ የተሰኘውና አይሲ ፐብሊኬሽን በተባለው ኩባንያ አማካይነት የሚታተመው መጽሔት በሚያወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥም ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ባንኮች ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፡፡ አዋሽና ዳንሸን በተካተቱበት በዚህ መጽሔት ሰንጠረዥ ውስጥ ወጋገን ባንክም ተካቷል፡፡ መጽሔቱ በአፍሪካ ቀዳሚ 100 ባንኮች ካላቸው ውስጥ ንግድ ባንክ 99 ደረጃ የተሰጠው ሲሆን፣ መጽሔቱ የተጠቀመበት አኃዝ የቆየ መሆኑም ተስተውሏል፡፡ ይሁንና ባንኩ በምሥራቅ አፍሪካ ከቀዳሚነት ከሚጠቀሱ 25 ባንኮች ውስጥ 14ኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አዋሽ፣ ዳሸንና ወጋገን የምሥራቅ አፍሪካ ባንኮች ደረጃ ውስጥ ለመካተት ችለዋል፡፡

  ከዚህ ባሻገር ግን ሁለቱም መጽሔቶች በተደጋጋሚ የኬንያውን ኢኪዩቲ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ያቀረበውን ተደጋጋሚ ጥያቄ አስተጋብተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች በፋይናንስ መስክ መሠማራት እንደማይችሉ የተከለከለ በመሆኑ መግባት አለመቻሉን የገለጹው የኬንያው ባንክ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁን ደረጃ በመያዝ ቀዳሚ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው፡፡ በሩዋንዳ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በታንዛንያና በኡጋንዳ እህት ባንኮችን የሚያንቀሳቅሰው ኢኪዩቲ ባንክ፣ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ጠቅላላ ሀብት ያለው ተቋም ነው፡፡

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች