Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊከንቲባ ድሪባ ለፀደቀው ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አቋቋሙ

  ከንቲባ ድሪባ ለፀደቀው ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አቋቋሙ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቅርቡ የፀደቀውን ማስተር ፕላን እንዲቆጣጠርና አፈጻጸሙንም እንዲከታተል ለተቋቋመው ፕላን ኮሚሽን አማካሪ ቦርድ አቋቋሙ፡፡

  ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ2009 ዓ.ም. መጨረሻ ያፀደቀው የአዲስ አበባ ከተማ አሥረኛው ማስተር ፕላን በይፋ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡

  ይህንን ማስተር ፕላን የማስፈጸም ኃላፊነቱ የሁሉም መሠረተ ልማት ተቋማት ቢሆንም፣ ተግባራዊነቱን የመቆጣጠርና የመከታተል ሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን ኮሚሽን ነው፡፡ ኮሚሽኑ ሥራዎቹን በሚያካሂድበት ወቅት ጠቃሚ ሐሳብ እንዲያመነጭና እንዲያማክር 22 አባላት ያሉት ቦርድ ተቋቁሟል፡፡

  ከንቲባ ድሪባ ከሁለት ሳምንት በፊት በጻፉት ደብዳቤ የከተማው ፕላን ኮሚሽን ራሱን የቻለ ሐሳብ የሚያመነጭና የሚያማክረው ቦርድ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡ ከንቲባው በጻፉት ደብዳቤ ጨምረው እንደገለጹት፣ ሐሳብ ለሚያመነጨውና ለሚያማክረው ቦርድ 17 ከፌዴራል፣ ከአዲስ አበባና ከሙያ ማኅበራት የተውጣጡ ተቋማት በኃላፊዎቻቸው አማካይነት ይወከላሉ፡፡ ከእነዚህ ተቋማት በተጨማሪም አምስት ግለሰቦች በቦርዱ ውስጥ ተካተዋል፡፡

  በቦርዱ ውስጥ የተካተቱት ግለሰቦች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሐሳብ በማቅረብና በመጻፍ የሚታወቁት ዳንኤል ክብረት (ዲያቆን)፣ የሥነ ልቦና ባለሙያው ምሕረት ደበበ (ዶ/ር) የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሽዮሎጂ መምህር የራስወርቅ አድማሴ (ዶ/ር) እና የሕግ ባለሙያና  ተንታኝ አቶ አብዱ ዓሊ ሂጅራ ናቸው፡፡

  ከንቲባ ድሪባ ለተቋማቱ ኃላፊዎችና ለግለሰቦች በጻፉት ደብዳቤ ‹‹እርስዎ ካለዎት ኃላፊነት፣ የሙያ ብቃትና ልምድ አንፃር ለአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን ሐሳብ አመንጪና አማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ለሦስት ዓመት እንዲሠሩ ተመርጠዋል፤›› በማለት ከንቲባው ገልጸዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 48/2009 የተቋቋመ ሲሆን፣ ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመውን ይህን ተቋም የማስተር ፕላን ዝግጅቱን ሲመሩ የቆዩት አቶ ማትዮስ አስፋው እንዲመሩት ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

  ማስተር ፕላኑ ለሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ በተለይ ሰፋፊ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎች፣ የፓርኮችና የአረንጓዴ ቦታዎች ልማት፣ እንዲሁም በመሬት አጠቃቀም ላይ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ግዙፍ ዕቅድ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

  ሐሳብ የሚያመነጩና የሚያማክሩ ቦርድ አባላት ውስጥ የተካተቱ ተቋማት በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቢሆኑም፣ ግለሰቦቹ የተመረጡበት መንገድ ግን ግልጽ እንዳልሆነላቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ አቶ ማቴዎስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

  መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ...

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...