Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ጋሻው ደበበ በምክር ቤቱ ቦርድ ከኃላፊነታቸው መታገዳቸው ከተሰማ ከሁለት ሳምንት በኋላ፣ የሥራ መልቀቂያ በማስገባት በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

  የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ ዋና ጸሐፊው ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ ውሳኔ በማሳለፉ ይህንንም ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አፈወርቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህ ውሳኔ ሳይፈጸም ቆይቶ አቶ ጋሻው ደበበ ማክሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም. መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡

  በዚሁ ዕለት የዋና ጸሐፊውን የመልቀቂያ ደብዳቤ የተቀበለው ቦርዱ፣ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በመጻፍ አሰናብቷቸዋል፡፡

  ሪፖርተር ማረጋገጥ እንደቻለው ዋና ጸሐፊው ቀደም ሲል በቦርዱ መታገዳቸው ከተሰማ በኋላ፣ እሳቸው ስለመታገዳቸው የሚገልጸው ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ታውቋል፡፡

  አቶ ጋሻውም የዕገዳ ደብዳቤው ስላልደረሳቸው በሥራ ገበታዬ ላይ አለሁ ብለው በሪፖርተር ላይ ማስተባበያ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡

  ይሁን እንጂ ይህንን በሥራ ገበታቸው ላይ መኖራቸውን የሚገልጸው መልዕክት ባስተላለፉ በቀናት ልዩነት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን አቅርበው ቦርዱም ወዲያውኑ ምላሽ በመስጠት አሰናብቷቸዋል፡፡

  አቶ ጋሻው ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ቦርዱ እኔን ስለማገዱ የሚገልጽ መረጃ የሌለ ቢሆንም፣ ለእኔ ግን ከሥራ በፈቃዴ መልቀቅ አስፈላጊ በመሆኑ መልቀቂያዬን አስገብቻለሁ፤›› ብለዋል፡፡ በአቶ ጋሻው ጉዳይ እንደ ሲዳ ያሉ ድርጅቶች የንግድ ምክር ቤቱን ማብራሪያ ጠይቀው እንደነበርም ይታወቃል፡፡ በወቅቱም የቦርዱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን ለቀረበው የማብራሪያ ጥያቄ የተሟላ መልስ መስጠት ተቸግረው ነበር፡፡

  ሪፖርተር እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው ዘገባ፣ አቶ ጋሻው በቦርዱ ውሳኔ መታገዳቸውን አስነብቦ ነበር፡፡ ምንም እንኳ እሳቸው ‹በሥራዬ ላይ ነኝ› ብለው ማስተባበያ ቢያቀርቡም፣ በመጨረሻ በራሳቸው ውሳኔ መልቀቂያ አስገብተው ተሰናብተዋል፡፡

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች