Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ለመሄድ ከቤት ሊወጡ ሲሉ ሚስታቸው አገኟቸው]

  • ወዴት ልትሄድ ነው?
  • ወደ ቢሮ ነዋ፡፡
  • እንደዚህ ሆነህ?
  • አዎና ምን ችግር አለው?
  • እየቀለድክ ነው?
  • ኧረ እውነቴን ነው፡፡
  • ዛሬ እኮ ዊኬንድ አይደለም፡፡
  • አውቃለሁ፡፡
  • ታዲያ ምን ሆነህ ነው ቁምጣና ቲሸርት አድርገህ ወደ ቢሮ የምትሄደው?
  • ምን ችግር አለው?
  • ፕሮቶኮል የሚባል ነገር አለ እኮ፡፡
  • አንቺ ዜና አትከታተይም ማለት ነው?
  • የምን ዜና?
  • ዓለማችንን እኮ ‘climate change’ እያስቸገራት ነው፡፡
  • እና ቢያስቸግራትስ?
  • እኛም ‘style change’ ማድረግ አለብና፡፡
  • አብደሃል ልበል?
  • ምን ነካሽ አንቺ ራስሽ ነጠላና ሻሽን ለውጠሽ ቀለል ያለ ልብስ መልበስ መልመድ አለብሽ፡፡
  • ለምን ተብሎ?
  • መድኃኒቱ እሱ ነው፡፡
  • ለምኑ?
  • ለ‘climate change’ የሚያስፈልገው  ‘style change’ ነው አልኩሽ እኮ፡፡
  • ለመሆኑ ገብቶሃል?
  • ምኑ?
  • ‘Climate Change’ ምን ማለት መሆኑ?
  • የአየር ንብረት ለውጥ ነዋ፡፡
  • ለነገሩ ቢገባህ ኖሮ ሳሪስ አትቀርም ነበር፡፡
  • የት እንዲሄድ ፈልገሽ ነው?
  • ፓሪስ ነዋ፡፡
  • ነገረኛ ነገር ነሽ፡፡
  • እውነት ግን ‘climate change’ ምን እንደሆነ የገባህ አልመሰለኝም፡፡
  • እንዲያውም ምን እንደምፈልግ ታውቂያለሽ?
  • ምንድን ነው የምትፈልገው?
  • ቢሮዬ ራሱ ቢች ዳር እንዲሆን ነው የምፈልገው፡፡
  • እውነትህን ነው?
  • የምሬን ነው የምልሽ፡፡
  • ታዲያ ለምን አታደርገውም?
  • ሰው እንደ አንቺ አይገባውማ፤ እብድ ነህ ነው የሚለኝ፡፡
  • እውነትም እብድ ነህ እኮ፡፡
  • ለነገሩ እኔ መፍትሔ አለኝ፡፡
  • ምንድን ነው መፍትሔው?
  • የራሴን ቤት ቢች ዳር መሥራት፡፡
  • ከየት አምጥተህ ነው የምትሠራው? ደመወዝህን ረሳኸው እንዴ?
  • ደመወዜ ትንሽ ቢሆንም ገቢዬ ከፍተኛ ነው፡፡
  • እንግዲህ እንደለመድከው ሙስናህ ውስጥ ተዘፈቅ፡፡
  • አትሳሳቺ፡፡
  • እንዴት?
  • እኔ ለሕዝብ እሠራለሁ፡፡
  • እሺ፡፡
  • ሕዝቡ ለእኔ ቤት ይሠራል፡፡
  • አልቀረብህም፤ ለማንኛውም ባለፈው የነበረብህን ግምገማ አስታውሰው፡፡
  • እሱማ አለፈ፡፡
  • ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም፡፡
  • እስኪመጣ እዘጋጅበታለሁ፡፡
  • ለማንኛውም ቢች ዳር ቤት ሠርቼ እገባለሁ ስትል ሌላ ቦታ እንዳትገባ፡፡
  • ሌላ የት?
  • ቂሊንጦ!

   

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚስታቸውን ምክር ሰምተው ፕሮቶኮላቸውን ጠብቀው ወደ ቢሮ ገቡ፡፡ አማካሪያቸው ቢሯቸው ገባ]

  • ምን እያነበቡ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት ያወጡትን መጽሐፍ እያነበብኩ ነው፡፡
  • እንዴ ምነው?
  • እንዲያውም ሁሉንም ለማንበብ እየተዘጋጀሁ ነው፡፡
  • እኮ ምን ተገኘ ብዬ ነው?
  • ምን ነካህ ነግ በእኔ ነው እኮ፡፡
  • ለነገሩ የአሁኑ መንግሥት ባለሥልጣናት ራሳቸው መጽሐፍ እየጻፉ ነው፡፡
  • እሱን ነው የምልህ፣ እኔም ላይ ሊጻፍ ይችላል፡፡
  • እርስዎ ላይ ምን ይጻፋል?
  • ሙሰኛ ነው፣ ኪራይ ሰብሳቢ ነው ኧረ ስንቱ፡፡
  • እርስዎ ግን እንደዚሁ አይደሉም፡፡
  • በቃልማ እንደዚህ ትላላችሁ፤ የምትጽፉት ግን ሌላ ነው፡፡
  • እኔ እኮ መጽሐፍ እየጻፍኩ አይደለም፡፡
  • ቢሆንም ለሚጽፉት እንደዚያ ብለህ መናገርህ አይቀርም፡፡
  • ኧረ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን፡፡
  • ብቻ ለማንኛውም መዘጋጀቱ አይከፋም፡፡
  • ምንድን ነው የሚዘጋጁት?
  • ሊጽፍብህ የሚችለው ሰው ላይ ቀድመህ መልስ ማዘጋጀት፡፡
  • ለማንኛውም እኔ የመጣሁት ለሌላ ጉዳይ ነው፡፡
  • ለምን ጉዳይ?
  • የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል አስመልክቶ እንድንነጋገር ብዬ ነው፡፡
  • ምን ንግግር ያስፈልገዋል?
  • ስለአጠቃላይ ሁኔታው ነዋ፡፡
  • ድል ያለ ድግስ መደገስ አለበት፡፡
  • የምን ድግስ?
  • የበዓሉ ድግስ ነዋ፡፡
  • አሁን ድግስ የምንደግስበት ወቅት ነው ብለው ነው?
  • ለምንድን ነው የማንደግሰው?
  • ያው አገሪቱ ድርቅ ላይ ናት ብዬ ነዋ፡፡
  • ይህ በዓል እኮ ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡
  • አውቃለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ሲባል እኮ ነው ጫካ የነበርነው፡፡
  • እሱማ ግልጽ ነው፡፡
  • የዚያ ሁሉ ሰው አጥንት የተከሰከሰውና ደም የፈሰሰው ለዚህ በዓል ነው፡፡
  • እኮ እሺ እንዴት ይከበር?
  • ቲሸርትና ኮፍያ መቅረት የለበትም፡፡
  • ተሳታፊዎቹ ለምን የራሳቸው የባህል ልብስ ለብሰው አይወጡም?
  • እሱማ አይሆንም፡፡
  • እኮ ለምን?
  • ብሔር ብሔረሰቦቹ እኩል መሆናቸውን ማረጋገጫው የሚለብሱት ቲሸርትና የሚያደርጉት ኮፍያ አንድ ዓይነት መሆኑ ነው፡፡
  • አዋቂ ነዎት እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስለዚህ አሁን በአስቸኳይ ይታዘዙ፡፡
  • ጨረታ ይውጣ አይደል ክቡር ሚኒስትር?
  • የምን ጨረታ ነው?
  • ለቲሸርቱና ለኮፍያው ነዋ፡፡
  • እናንተ ሰዎች በጨረታ አብዳችኋል እንዴ?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • 200 ቶን ብረት እንግዛ ሲባል ጨረታ ትላላችሁ?
  • እ…
  • 500 ኩንታል ሲሚንቶ እንግዛ ሲባል ጨረታ ትላላችሁ?
  • ታዲያ ምን እናድርግ መመርያው እኮ ያስገድደናል?
  • ለማንኛውም ይህ የሕዝብ በዓል ስለሆነ ጨረታው ይቅር፡፡
  • የፋይናንስ ክፍሎች እኮ እሺ አይሉንም፡፡
  • የፋይናንስ ኃላፊውን ጥራልኝ፡፡

  [የፋይናንስ ክፍል ኃላፊው ቢሯቸው ገባ]

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • በዓሉ እየደረሰ እንደሆነ ታውቃለህ?
  • የትኛው በዓል ክቡር ሚኒስትር?
  • የትኛው እንድልህ ፈልገህ ነው?
  • የክርስቶስ ኢየሱስ የልደት በዓል፤ ማለቴ ገናን ነው የሚሉኝ?
  • የለም የለም፤ እኛ የምናከብረውን ነው እንጂ?
  • እኮ የትኛው?
  • የብሔር ብሔረሰቦች በዓልን ነዋ፡፡
  • እሱማ እንደደረሰ አውቃለሁ፡፡
  • ይህን በዓል ለየት አድርገን ነው ማክበር ያለብን፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • በቃ በዓሉ የሕዝብን እኩልነት የሚያሳይ ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡
  • እሱማ ይታወቃል፡፡
  • ስለዚህ ካለፈው ዓመት በተለየ ማክበር አለብን፡፡
  • ለምን ሲባል?
  • ሕዝቡ እንዳይሰለቸን ነዋ፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • በምርጫው ውጤት ራሱ ይኼን ማወቅ ትችላለህ፡፡
  • እንዴት?
  • 99.6 በመቶ የነበረውን ወደ መቶ በመቶ ባናሻሽለው ኖሮ ሕዝቡ ይሰለቸን ነበር፡፡
  • ለዚያ ነው የደፈናችሁት?
  • ያለበለዚያ ሕዝቡ ይሰለች ነበር፡፡
  • ስለዚህ በዓሉ እንዴት ይከበር?
  • ማስታወሻ ያዝ፡፡
  • እሺ፡፡
  • የሚገዙ ነገሮችን ልንገርህ፡፡
  • ይቀጥሉ፡፡
  • ቲሸርት፣ ኮፍያ፣ እስክሪብቶና ማስታወሻ ደብተር አይቀሩም፡፡
  • እነዚህ ለነገሩ ባለፈውም የነበሩ ናቸው፡፡
  • አሁን ለየት ለማድረግ አንድ ነገር መጨመር አለብን፡፡
  • ምን ይጨመር?
  • ጫማ ይሠራ፡፡
  • ለተሳታፊዎቹ?
  • አዎና፡፡
  • ስንት ቁጥር ጫማ?
  • በሁሉም ዓይነት ቁጥር አንድ ዓይነት ጫማ ይሠራ፡፡
  • ከልብዎት ነው አይደል ክቡር ሚኒስትር?
  • አንተ የታዘዝከውን ብቻ ፈጽም፡፡
  • ማን ነው የሚሠራው?
  • እሱን ለእኔ ተወው፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ጋ ደውለው፣ ቢሯቸው እንዲመጣ ነግረውት መጣ]

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ጮማ የሆነ ሥራ አግቼልሃለሁ፡፡
  • እርስዎ ራሱ ጮማ ነዎት እኮ፡፡
  • ያው በዓላችንን ልናከብር ነው፡፡
  • የትኛውን በዓል ክቡር ሚኒስትር?
  • የብሔር ብሔረሰቦችን ነዋ፡፡
  • እሺ ምን ልታዘዝ?
  • ቲሸርትና ኮፍያ ትሠራለህ አይደል?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እስኪብርቶና ማስታወሻ ደብተርስ?
  • እርሱንም መሥራት አያቅተኝም፡፡
  • የዚህን ዓመት በዓል ግን ለየት ለማድረግ ጫማን አስገብተንበታል፡፡
  • እኔ እኮ ጫማ አልሠራም፡፡
  • ጅል ነህ ልበል?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • አሁኑኑ ሄደህ ፈቃዱን አታወጣም እንዴ?
  • በዓሉ የቀረው እኮ አጭር ጊዜ ነው፡፡
  • ሰውዬ ይኼን አጋጣሚ ተጠቅመህ እኮ ነው ከአስመጪነት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ መግባት የምትችለውም፡፡
  • እውነትዎትን ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • እኔ ውሸት አውቃለሁ?
  • ኧረ በፍጹም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስለዚህ ቶሎ ብለህ ጫማውን ለመሥራት ተዘጋጅ፡፡
  • ለመሆኑ ምን የሚባል ጫማ ነው የምሠራው?
  • ለስሙ አታስብ እኔ አሪፍ ስም አለኝ፡፡
  • ምን የሚል?
  • ብሔር ብሔረሰቦች!

   

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  በቴሌ ብር የማይሠሩ ማደያዎች ቀነ ገደብ ተቀመጠባቸው

  ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለመሥራት እየመከረ ነው በኢትዮጵያ...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የማስተማር ሙያ ሥልጠና ባልወሰዱ መምህራን ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ተላለፈ

  ለአሥር ዓመት ሥልጠናውን ያልወሰዱ መምህራን ከመምህርነት ሙያ ይወጣሉ የግል ትምህርት...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...

  የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ምሥረታና ተጠባቂ ዕድሎቹ

  ነፃ የንግድ ቀጣናዎች የልዩ ኢኮኖሚ ቀጣናዎች አካል ሲሆኑ፣ በውስጣቸው...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...