Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናኢትዮጵያ በግብፅ ሥጋቶች ላይ ምላሽ ይዛ ለመቅረብ ተስማማች

  ኢትዮጵያ በግብፅ ሥጋቶች ላይ ምላሽ ይዛ ለመቅረብ ተስማማች

  ቀን:

  የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓርብና ቅዳሜ በሱዳን ባደረጉት ስብሰባ ኢትዮጵያ በግብፅ ለተነሱ ሥጋቶች ከሁለት ሳምንት በኋላ ምላሽ ይዛ ለመቅረብ ተስማማች፡፡

  ሦስቱ አገሮች ላለፉ ዘጠኝ ስብሰባዎች በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴዎቻቸው አማካይነት ሲወያዩ የቆዩ ቢሆንም፣ የታላቁን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እንዲያጠኑ በተመረጡ ሁለት ኩባንያዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ ጊዜ ፈጅቶባቸዋል፡፡

  ይህ አሳስቦኛል የምትለው ግብፅ ቀጣዩ ስብሰባ ከሦስቱም አገሮች በሚወከሉ ሁለት ሁለት ሚኒስትሮች አማካይነት ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሄድ በጠየቀችው መሠረት ነው ውይይቱ የተካሄደው፡፡

  በግብፅ በኩል በዋናነት ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከውይይቱ ጋር ሲነፃፀር በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ፣ ውይይቱ መስመር እስኪይዝ ድረስ ግንባታው እንዲቆም ጥያቄ አቅርባለች፡፡

  አሁን አለመግባባት የፈጠሩት ኩባንያዎችን  ከማግባባት ውጪ ሌሎች ኩባንያዎችን ማወዳደር ተብሎ የቀረበው ሐሳብ አሁንም ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ፣ ግብፅ እንደ ተቃወመችው ለማወቅ ተችሏል፡፡

  በመሆኑም የግብፅ ማጠንጠኛ ሐሳብ አሁን ያለው የቴክኒክ መመርያ ማለትም ሦስቱ አገሮች የተስማሙበት 70 በመቶ የፈረንሣይ ኩባንያ ቢአርኤል ኢንጂነርስ የጥናት ድርሻ፣ እንዲሁም 30 በመቶ የኔዘርላንድ ኩባንያ ዴልታ ሬዝ የጥናት ድርሻ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ፣ ሁለቱም ኩባንያዎች እኩል የመወሰን ነፃነት ኖሯቸው ጥናቱ እንዲጀመር ግፊት የማድረግ እንቅስቃሴ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

  በኢትዮጵያ በኩል የግድቡ ግንባታ ይቁም በሚለው ላይ ድርድር እንደማይደረግ ራሳቸው ግብፃውያንም ጭምር የሚያውቁት በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ በኩል ይህ ይሆናል ተብሎ እንደማይገመት ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

  ምናልባት የቴክኒክ መመርያው ላይ ማሻሻያዎች ለማድረግ ይቻል እንደሆነ ለማየት የጊዜ ቀጠሮው ተጠይቆ ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ይገምታሉ፡፡ ቀጣዩ የሦስቱ አገሮች ስድስት ሚኒስትሮች የሚገኙበት ስብሰባ በሱዳን ካርቱም ታኅሳስ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...