Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየመንግሥት ተቋማት የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተወሰነ

  የመንግሥት ተቋማት የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተወሰነ

  ቀን:

  እያንዳንዱ የመንግሥት ተቋም የራሱን የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ነድፎ ተግባራዊ እንዲያደርግ መንግሥት መወሰኑን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐሙስ ታኅሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ሦስተኛውን አገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጠቅላላ ጉባዔን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት፣ የመንግሥት ተቋማት የራሳቸውን የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ነድፈው ወደ ተግባር ለመሸጋገር የሚያስችላቸውን ሰነድ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡

  ስትራቴጂውን ወደ ተግባር በማሸጋገር ረገድ የየተቋማቱ ኃላፊዎችና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከፍተኛውን ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ መንግሥትም ከተጠያቂነት ጋር አስተሳስሮ በጥብቅ የሚከታተለው መሆኑን አቶ ኃይለ ማርያም አስገንዝበዋል፡፡

  እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ በተወሰኑ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ተቋማት ብቻ ሙስናን መከላከልና መዋጋት የሚፈለገውን ውጤት አያስመዘግብም፡፡ በመሆኑም ፀረ ሙስና ትግሉን ወደ ሌሎችም አካላት ማስፋት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ተቋማት ዋነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ስትራቴጂ ነድፈው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በየተቋማቱ የሚስተዋሉትን የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫ የሆነውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው አስረድተዋል፡፡

  የፌዴራልም ሆነ የክልል ፀረ ሙስና ተቋማት ሕዝቡ በፀረ ሙስና ትግሉ ዙሪያ በቁርጠኝነት እንዲሠለፍ የማስተባበርና የመምራት ሚናቸውን እንዲያጠናክሩም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አሳስበዋል፡፡ ሙስናንና ኢሥነ ምግባራዊ ድርጊቶችን ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ ለመከላከልና ለመዋጋት፣ በሕፃናትና ወጣቶች ሥነ ምግባር ግንባታ ላይ ለመሥራት የተያዘው አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆን መረባረብ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

  ለሁለት ቀናት የቆየውን ሦስተኛውን አገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጉባዔ፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን በንግግር ሲከፍቱ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ ሚኒስትሮችና በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...