Saturday, August 13, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊብሮድካስት ባለሥልጣን ሬዲዮ ጣቢያዎች በኦሮሚያ ያለውን አለመረጋጋት በጥንቃቄ እንዲዘግቡ እየተከታተልኩ ነው አለ

  ብሮድካስት ባለሥልጣን ሬዲዮ ጣቢያዎች በኦሮሚያ ያለውን አለመረጋጋት በጥንቃቄ እንዲዘግቡ እየተከታተልኩ ነው አለ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ሬዲዮ ጣቢያዎች በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አለመረጋጋት እንዳይባባስ ተጠንቅቀው እንዲዘግቡ እየተቆጣጠረ መሆኑን አስታወቀ፡፡

  የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶምና የሥራ ባልደረቦቻቸው የ2008 ዓ.ም. የሥራ ዕቅድና የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለፓርላማው የባህል ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡

  የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ፈቲያ የሱፍ፣ ‹‹ዓባይ የተባለ ሬዲዮ ጣቢያ ስሜት ቀስቃሽ የኦሮሚያ ዘፈኖችንና የቴዲ አፍሮ ዘፈንን ሲያሰማ እንደነበር ጥቆማ ደርሶኛል፤›› ካሉ በኋላ፣ ባለሥልጣኑ እንደዚህ ዓይነት የሚዲያ ሥርጭትን በመቆጣጠር ረገድ ምን እየሠራ እንደሆነ እንዲያብራሩ ጠይቀዋል፡፡

  የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም ‹‹ዓባይ›› የተባለው ሚዲያ የተባለውን ሊያደርግ ይችላል ብለው ለማመን እንደሚቸግራቸው፣ ነገር ግን እንደሚያጣሩት ከገለጹ በኋላ በጥቆማ ደረጃ የሰሙት ‹‹ሸገር ሬዲዮ ጣቢያ›› እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  በዚህ ሳምንት ውስጥ ሁሉንም ሬዲዮ ጣቢያዎች በጉዳዩ ላይ ሰብስበው እንዳነጋገሩና ማስጠንቀቂያ እንደሰጡም አቶ ዘርዓይ አስረድተዋል፡፡

  በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ምንጮች በዚህ ሳምንት ከብሮድካስት ባለሥልጣን በቀረበ ጥሪ በጉዳዩ ላይ ውይይት ተካሂዶ እንደነበር አረጋግጠዋል፡፡

  ሸገር ሬዲዮ ባስተላለፈው አንድ ዜና ላይ የአማራና የኦሮሞ ብሔሮች ተጋጭተዋል ተብሎ መገለጹ አግባብ አለመሆኑ በወቅቱ እንደተገለጸ አስታውሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሸገር ተወካዮች በኩልም ጣቢያው ኃላፊነት የሚሰማው ስለመሆኑ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ሌላው የተነሳው ጉዳይ በግጭቱ ዙሪያ ተገቢውን ሽፋንና ሕዝቡን የማወያየት ሥራ ጣቢያዎቹ እንደማይሠሩ፣ በተለይ ብስራት ሬዲዮ ጣቢያ ስፖርት ላይ ብቻ ማተኮሩ መተቸቱንና ፋና ደግሞ ሽፋን እየሰጠ ስለመሆኑ እንጂ ስለሚለቀቁ ዘፈኖች አለመነሳቱን ገልጸዋል፡፡

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለሥልጣኑ በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ጣቢያ ለማቋቋም ለሚፈልጉ የግል ባለሀብቶች ፈቃድ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

  ኢቢኤስ የተባለው ጣቢያ ከአሜሪካ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ፣ ከኢትዮጵያ አቅሙ ያላቸው ባለሀብቶች የጣቢያ ባለቤት እንዲሆኑ የቀረበውን ምክረ ሐሳብ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ቦርድ አፅድቆታል ሲሉ አቶ ዘርዓይ ገልጸዋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት በዚህ ሥራ ለመሳተፍ ብቁ የሚያደርጉ መመዘኛዎች እየተሠራ በመሆኑ፣ በመመርያ ደረጃ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡     

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...