ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16 አዳዲስ ሹመቶችን ካፀደቁ በኋላ እስከምሽት ድረስ ሌሎች ሹመቶችን ያሳውቃሉ በተባለው መሠረት የሚከተሉትን ዘጠኝ ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡
- ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
- ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
- አቶ አባዱላ ገመዳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ
- አቶ አህመድ አብተው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ሞገስ ባልቻ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ
- አቶ ዓለምነው መኮንን በሚኒስትር ማዕረግ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚደንት
- በቀለ ቡላዶ (ዶ/ር) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ያሬድ ዘሪሁን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል በመሆን ተሹመዋል፡፡