አስፈላጊ ግብዓቶች
- 1 ኪሎ የተፈጨ ሥጋ
- ½ ኪሎ የተፈጨ የዓሳማ ሥጋ
- 1 የተቀቀለ የአበባ ጎመን
- ¼ ኩባያ የተከተፈ ሽንኩርት
- 1 የሻይ ማንኪያ ሰናፍጭ
- 2 የተመታ እንቁላል
- 1 ኩባያ የተፈጨ ዳቦ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- ¾ ኩባያ ወተት፣ ቅርንፉድ፣ ቁንዶ በርበሬ፣ የአበባ ጎመን ወይም የተቀቀለ ካሮት ወይም አተር መጠቀም ይቻላል፡፡
አሠራር
- ከአበባ ጎመኑ በስተቀር ከላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ማደባለቅ፡፡
- መሀሉ ላይ ክብ የቅርፅ ማውጫ ባለው ቅባት የተቀባ መጋገሪያ ዕቃ ላይ መሙላት፡፡
- ሙቀቱ 350 ዲግሪ ፋራናይት በሆነ ምድጃ ለአንድ ሰዓት ተኩል ማብሰል፡፡
- ከበሰለ በኋላ ሎፉን ከመጋገሪያ ዕቃው ውስጥ አውጥቶ መሀሉ ላይ የአበባ ጎመኑን ማድረግ፡፡
አሥራ ሁለት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)