Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአምባሳደር ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ

  አምባሳደር ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ

  ቀን:

  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ (አምባሳደር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ፡፡ አቶ ግርማ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት፣ በቅርቡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙትን ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን (ዶ/ር) ተክተው ነው፡፡

  ከሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሠሩ በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) መሰየማቸው ታውቋል፡፡ አቶ ግርማ አምባሳደር ሆነው ወደ አሜሪካ ከመመደባቸው በፊት፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ለ15 ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱም የተሻለ እንቅስቃሴ በማድረግ የተለያዩ ለውጦችን ማስመዝገባቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የተቋሙ ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ተመልሰው የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑም አዲስ ስለማይሆኑ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

  አቶ ግርማ ሰብሳቢ ሆነው በተሰየሙበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ውስጥ፣ ሰሞኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ተሾመ ቶጋ (አምባሳደር)፣ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት ወልደሃና (ዶ/ር)፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ መስቀል ተፈራ፣ ዮሴፍ ረታ (ዶ/ር)  የቦርድ አባል ሆነው ተሰይመዋል፡፡ አቶ ግርማ በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታና በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...