Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊፖሊስ የታሰሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በሽብር ወንጀል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት ተናገረ

  ፖሊስ የታሰሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በሽብር ወንጀል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት ተናገረ

  ቀን:

  – ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀናት ተፈቀደለት

  ታኅሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት በፀጥታ ኃይሎች ወደ ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መወሰዳቸው የተገለጸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ በሽብር ወንጀል ድርጊት መጠርጠራቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

  የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ቡድን ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ታኅሳስ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጠርጣሪዎችን አቅርቦ ስለታሰሩበት ጉዳይ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪዎቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ሆነው ሌሎች አባላትን እየመለመሉ መሆናቸውንና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን በመጠቀም ግንኙነት እየፈጠሩ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም ሲዘጋጁ እንደተደረሰባቸውና በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ የሚቀረው ምርመራ እንዳለ በመጠቆምም የፀረ ሽብር ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀናት እንዲፈቀድለት አመልክቷል፡፡

  የተጠረጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አቶ ዳንኤል ተስፋዬና አቶ ሸዋታጠቅ ኃይለ መስቀል መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ዳንኤል እንደገለጸው፣ በቁጥጥር ሥር ውሎ ቤቱ ሲፈተሽ የተገኘው ባንዲራ፣ ሲዲና ስልክ ብቻ ናቸው፡፡ በመሆኑም መርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን ያህል ቀናት ሊፈቀድለት እንደማይገባ በመግለጽ ተቃውሟል፡፡

  አቶ ሸዋታጠቅ በበኩሉ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኢሕአዴግ ተደራጅቶ እየሠራ ነው፡፡ መርማሪ ቡድኑ ከገለጸው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለውና የተጠቀሰውንም ድርጅት እንደማያውቀው አስረድቷል፡፡ የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑን ጠቁሞ፣ የተጠየቀበትን ያህል ቀን ሳይሆን አጭር ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

   የፓርቲው ልሳን ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ይዝቱበት እንደነበር፣ ቤቱ ሲፈተሽ የተገኘው የሰማያዊና የመድረክ መግለጫዎችና ፕሮግራሞች መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ፕሮግራሞቹና መግለጫዎቹም ከሕጋዊ ፓርቲዎች የተገኙ መሆናቸውንና እሱ የታሰረውም ጋዜጠኛ በመሆኑ ብቻ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

  ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የተጠርጣሪዎቹን ተቃውሞ በማለፍ መርማሪ ቡድኑ የጠየቀው 28 ተጨማሪ ቀናት ፈቅዶ ለጥር 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ አቶ ፍሬው ተክሌና አቶ ቴዎድሮስ አስፋው የተባሉት የፓርቲው አባላትም ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት ተጠይቆባቸው እንደተፈቀደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...