Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ታሰሩ

  የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ታሰሩ

  ቀን:

  በቅርቡ ምክንያታቸውን ሳይገልጹ ከሰማያዊ ፓርቲ መልቀቃቸውንና የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል አለመሆናቸውን በፌስቡክ አድራሻቸው ያስታወቁት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. መታሰራቸው ታወቀ፡፡

  አቶ ዮናታን ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በመደበኛ የማስተማር ሥራቸው የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ አስተምረው እንደጨረሱ ለዕረፍት ወጣ ብለው ሳይመለሱ መቅረታቸውን፣ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቅርብ ጓደኞቻቸው ገልጸዋል፡፡

  አቶ ዮናታን ያለወትሯቸው ለዕረፍት እንደወጡ ሳይመለሱ ቢቀሩም ብዙም ትኩረት እንዳልሰጡት የገለጹት ጓደኞቻቸው፣ አመሻሹ ላይ ቤተሰቦቻቸው በሞባይል ስልካቸው ሲደውሉ ዝግ እንደሆነ ነግረዋቸው የት እንደሄዱ ወይም አብረዋቸው ከሆኑ እንዲነግሯቸው ሲጠይቋቸው እነሱም መደናገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በጋራ ወደሚያውቋቸው ሁሉ ሲደውሉ ‹‹የለም፣ አላየነውም፣ አልተደዋወልንም…›› ከሚሉ መልሶች ውጪ ዓይተናቸዋል የሚል ሳያገኙ እንደቀሩ አስረድተዋል፡፡

  አቶ ዮናታን ታኅሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በፖሊሶች ታጅበው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሄደው እንደነበርና ቤታቸው መፈተሹም ታውቋል፡፡ በምን ምክንያትና ለምን እንደታሰሩ ግን ገና አለመታወቁን፣ አሁን የሚገኙት በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  አቶ ዮናታን ከሰማያዊ ፓርቲ ለምን እንደለቀቁ በተለያየ ጊዜያት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...